Melkamu Temesgen: የግዕዝ ፍደል ጥየቄ እና Afaan Oromoo

የግዕዝ ፍደል ጥየቄ እና Afaan Oromoo

By Melkamu Temesgen

(Via Gullelepost Facebook)

ለዶ/ር አበራ ሞላ፡ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ ፕሮፌሰር ማሞ ሙጨ፣ ዶ/ር ባዬ ይማም፣ፕሮፌሰር ኃይሌ ላረቦ፣አቶ ግርማ ሰይፉ፣አቶ ያሬድ ጥበቡ፣አቶ ተፈራ ድንበሩ ፣ለግርማ ካሳና ለተቀሩት የቡድናችሁ አባሎች በሙሉ ሰለምታዬ ይቀድማል።
በመጀመርያ የገረመኝ ነገር የእናንተ ቡድን አባላት በተለያዩ ሀገሮች ማለትም ኢትዮጵያ፣አሜርካና አውሮፓ የሚኖሩ ሆነው ሳሉ፣ አስደና ቂናእጅግ ስበዛ ለትዝብት በምዳርግ መልክ ፣ምናልባት አየር ባየር ተገናኝታችሁ Afaan Oromoo በአማራ ክልል በግዕዝ ተደግፎ ትምህርት እንዲሰጥ ለአማራ ብሔራዊ ክልል ፕረዜዳንት ለተከበሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ደብዳቤ ከፃፋችሁ ሰነባብቷል።ለወደፍት ክቡር አቶ ገዱ የሚሰጧችሁን መልስ እኔም በጉጉት እየጠበኩኝ ነው።ይሁንናከመቶ አለቃ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ሌላ፣ሌሎች ተማርከው የሰነበቱ ጄኔራሎችም ድጋፋቸውን እያሳዩ ስለመጡ የሚከተለውን ለማለት ፈለኩ።

1ኛ/እናንተን ዲያቁኑ ግርማ ካሣ ሰብስቦአችሁ፣ስማችሁን በዝርዝር ጽፎ ሁልጊዜ ያደርግ እንደነበረው ሁሉ በፀረ ኦሮሞ አቋሙ ስላሰለፋችሁ፣የግርማ የሚቀጥለውን ሙያዊ የእድገት እርከን ከዲያቁን ቅስና መሆኑ ቀርቶ እሱም ዶ/ር ፕሮፌሰር ይባል ዘንድ
እደግፋሌሁ።ምርምሩን ጨርሷልና።ግርማ ካሣ በአንድ ወቅት ስጽፍ “ኦሮሞዎች ሥልጣን ከሚይዙ፣ህወሃት ዕድሜ ልኩን ኢትዮጵያን ቢገዛ እመርጣሌሁ” ያለ ሰው ነው።በሌላ ጽሁፉም ላይ “አምስት ሚሊዮንየሚሆኔው የአዲስ አባባ አካባቢ ነዋሪውን ኦሮሚያ የሚሉት ሰዎች፣ገፍተውት ወደ ጎንደርና ጎጃም ሊጥሉ ወይም ሊፈጁት ነው፣ለዚህ ነው ኦሮሚያ የሚሉት..” ብሎ አስነብቦናል። በግርማ አባባል የምፈጁትና የሚገፉት ኦሮሞዎች የሚፈጁትና የሚገፉት አማሮች ናቸው። ጉደኛው ግርማ ካሳ”በ 5/8ዬ የኦሮሞ ደም አለኝ”ስል የነበረ ሰው፣ለካ 3/8 ደሙ ሌላ ዘር ሆኖ የቀረው በኦሮሞ ጥቃት ነው ፣ማለት ነው።

2ኛ/ከግርማ ጋር ተመሳሳሳይ አቋም ያለው አቶ ያሬድ ጥበቡ በአንድ ወቅት “..የአዲስ አባባ ማዛጋጃ ቤትን ማዕከል ያደረገ በሁሉም አቅጣጫዎች 150ኪ/ሜ ሬድየስ ያለውን መሬት 10ኛ ክልል ማደረግ ነው…” በማለት ኦሮሚያን በምዕራብና በምሥራቅ ቆርጦ ከመሃሉ ሌላ ክልል ለመፈጠር ምኞት አለው። እንደ ማስቴር ፕለኔ.. አባይ ፀሐዬ ማለት ነው።በዕርግጥም መለስ ስሞት” ኢትዮጵያ ድንቅ ሰው አጣች”በማለቱ አማሮች እስከ ዛሬ እየወረዱበት ነው።

3ኛ/የቀድሞው የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ Qubee ላይ ብቻ ሳይሆን Afaan Oromoo መነገሩንም አይፈልጉትም።”..የአክስቴን ልጅ ከሰንዳፋ አንድ ጥያቄ ጠየቄው ነበር፣ለመሆኑ ለምን በአማርኛ የሚያስተምሩበት ት/ቤት ገብተህ አትማርም? ስለው ..ጋሼ ቦኃላ ሥራ አላገኝም አለኝ ” ብለው ስለመናገራቸው ከዚህ ቀደም  እኔም መጥቀሴን አስታውሳሌሁ።ይህችን ጽሑፍ ከመጀመሬ በፍት፣በህብረ ራዲዮ ቃለ ምልልስ፣ የቀድሞው የድህንነት ሹም አቶ አያሌው መንገሻ ፣አቶ ግርማ ሰይፉን በምረጫ ወቅት አንድ ብቸኛ ነጻ ሰው አስመስሎ ፖርላማ እንዲገባ የተደረገው የኢህአዴግ አባል ባልሆኑ የመረጃ መዋቅሮች ውስጥ የታቀፈና መረጃ ያቀርብ ስለነበረ ነው፣ለዚሁም መሰረጃው ስለ አቶ ግርማ ፖርለማ መግባት ፣ደረብጽዮን የመረጃ ሹሞች ስብሰባ ላይ በዝርዝር የገለፀ ሲሆን፣ከሚከፈለውም ገንዘብ ጨርቆስ አካባቢ ዘመናዊ ሱቆች፣በድሬደዋ ትልቅ ሆቴል አለው። አቶ ግርማ ሰይፉ የፓርላማ አባል ከነበሩት የህወሃት አባላትእኩል ሀብት ያለው ብቸኛ ሰው ነው” በማለት ያስረዳሉ።

4ኛ/ዶ/ር ኃይሌ ላረቦ ደግሞ በኢሳት ቀጥታ ስርጭት”ኦሮሞ የሚባል ህዝብ የለም “የሚል ሰው ነው።እንደዚህ አይነት ጥላቻ በህዝባችን
ላይ ያላቸው ሰዎችና አጋሮቻቸውን Qubee ላይ ዘመቻ ቢከፍቱ አይገርምም።በተነጥል የነሱን ጥላቻ ከመዘርዘር በግዕዝ Afaan Oromoo መጻፍ በቃላቶች ትርጉም ላይ ከፍተኛ ስህተትን፣የአባባል ለውጥን፣የንግግር ብልሽትንና ሊሳናዊ መዘበራረቅን እንደሚያስከትል ማሰረዳቱ ይመረጣል።ኦሮሞነት “አለብን” የሚሉት ግርማ ከሳ፣ግርማ ሰይፉም ሆኑ ያሬድ ጥበቡ ከቻሉ Qubee ይኼውላቸው! እነ ዶ/ር አበራና ዶ/ር ፍቅሬ “Qubee ቦታና ጊዜ ይፈጃል” ከማለት ኦሮሞ ነኝ ካሉ ትርጉም ሰጪነቱን፣አሻሚ ያለመሆኑንና ከስህተት የጻዳ ስንኝ ጽፈው ያመሳክሩ…እነ አብራሃም ቀጄላም እንዲሁ።

**** Qubee***

Abrahaam Qajeelaa ..በአማርኛው ቀጄላ ውሰጥ “ቀ” -“qe” ከሆኔ የአብራሃም አባት ስም Qejeelaa ሊሆን ነው። በግዕዝ “በ”ን በቀለ ውሰጥ እንደሚናነበው ከሆኔ ማለት ነው።ስለዚህ Qajeelaa የሚለውን ሀረግ ወይ ልናጠፈው ወይ Qejeela ብለን ቃሉን ልንለውጥ ነው።በግዕዝ “Dha”የሚል ባለመኖሩና ብቻ ሳይሆን አሁንም” በቀለ” ውስጥ በሚነበበው “በ” Badhaasa ብሎ “ስጦታ “ለማለት ላይቻል ነው።የበቀለው “በ” ..”Ba” ሆኖ Badhaasa ለማለት አይችልም። Dhaabaa.Dhaba,dhaaba,badhoo,badhaadhinaa,dhadhabinaa,dhaadhannoo የመሳሰሉትን እነ ግርማ ካሳ ጊዜ ወስደው እሰኪለማመዱት ወደ ሌላው።
A/ Faluu( ዘዴ መፈለግ)፣Faallu (መቃረን)፣Falluu (ዘዴ እንሻ) በግዕዝ ስጻፉ=ሶስቱም” ፋሉ” ይሆናሉ።ከሶስቱም “ፈለቀ” ውስጥ ባለው “Fe” ከሞከርነው ትርጉሙ Afaan Oromoo አይሆንም።
B/ Buti (ፈቅ አርገው)፣ Butii( ጠለፋ)፣Buutii ( እፍኝት) ሲሆን
በማናቸውም መንገድ በግዕዝ ስጻፍ=”ቡቲ” ይሆናል።”ቡት” ብሎ ከጻፈም በ”ቤት”ውሰጥ ያለው “ት” ይወሰድ ከተባለ “ቡት”-“But”
Afaan Oromoo አይደለም።
C/ Homaa (ምንም)፣Hooma(ሠረዊቱ፣መንጋው)፣ Hoomaa(ሠራዊት) =በግዕዝ ስጻፍ( ሆማ) ነው።ለምሳሌ “ሆመ” ብለህ በመልከሙ ስም ላይ ያለውን “መ”መጠቀም ትርጉም አልባ ይሆናል።
D/ Haadu( ቢላዋ)፣Haaduu(መላጨት)፣Haadduu(መላጫ) ሶስቱም በግዕዝ ስጻፍ=”ሃዱ” ነው።የትኛውን ቃል ይወክላል?
E/ Qufaa(ሳል)፣Quufa( ጥጋብ)፣Quufaa(ጥጋበኛው) በግዕዝ ሶስቱም “ቁፋ”ሆነው ይጻፋሉ።
F/ aduu(የፀሐይብርሃን)፣aaduu( ማቃሰት)፣aadduu(የሚታቃስት)
በግዕዝ ስጻፍ “ኣዱ”ብቻ አራቱን ትርጉሞች እንዴት ልገልጽ ይችላል?
G/ muudama (ለሥልጣን መታጨት)፣Muddama (አስቸኳይ) Muddamaa (የሚጣደፍ) ሶስቱም ትርጉሞች ስጻፉ “ሙዳማ” ሆነው ነው።በደበበ ውስጥ የመለው “ደ”የአነጋገር ግድደፈት፣
የትርጉምም መዛባት። ነወ።
H/ Sodaa (ፍርሃት)፣Soddaa(አማች) ሁለቱም በግዕዝ ስጻፍ “ሶደ” ሆኖ ነው።
I/ Xuxuu ( መምጠጥ)፣Xuxxuu( መጣጭ) በግዕዝ ስጻፉ ” ጡጡ”ይሆናሉ።
J/ Gobaa(ፍላጻ)፣Gobbaa(ሰብሰብ ያለ)፣Gooba(ሻኛ) ለሶስቱም የሚጻፈው “ጎባ” ነው። በቀለ ወረሰጥ ያለው ” በ” የትኛውም ትርጉም አይኖረውም።
K/ Gadi ( ታች)፣Gaddii( ዕጣ ፋንታ)፣Gaadi( በአይነ ቁራኛ ጠበቅ) በግዕዝ ስጻፉ ለገረመው የሚውለው “ገ” ከተወሰደ ተዛብቷል።
L/Guba ( ቃጣሎ)፣Gubaa( የሚያቃጥል)፣ Gubbaa(ከላይ) በግዕዝ መጻፍ ያለበት “ጉባ” ተብሎ ብቻ ነው።
M/ Uummani( ህዝቡ)፣Uumanii) (ፈጥረው)፣Uumaani( የፈጠረው) በግዕዝ “ኡማኒ”ይሆናል።
እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ መቶ ሺህ ነጥቦችን ማቅረብ ይቻላል። የሌላውን ህዝብ ለመጥላት የታሰበ፣ የተቀየሰ ወይም በሚስጢር የተያዘ ሴራ የለም። የራስህን ጣል የሚል ደግነትም አይኖርም።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s