ስለ ኢሬቻ ምስክርነት፡ ሰዎች በአጋጣሚ ተገፋፍተዉ ያለቁ ሳይሆን የታቀደና የተቀነባበረ ሴራ ሰለባ መሆናቸዉን የሚከተሉት 16 ነጥቦች ማሳያዎች ናቸዉ፤፤

#IrreechaMassacre 2016 Wittness

ስለ ኢሬቻ ምስክርነት፡ ሰዎች በአጋጣሚ ተገፋፍተዉ ያለቁ ሳይሆን የታቀደና የተቀነባበረ ሴራ ሰለባ መሆናቸዉን የሚከተሉት 16 ነጥቦች ማሳያዎች ናቸዉ፤፤

Related image

Via FaceBook

1. አካባቢዉን የማዘጋጀት ቅድመ-ዝግጅቱ፡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ለበአሉ ዝግጅት ተብሎ ለዘመናት ሲታጠር የነበረዉና ዘንድሮ (2016)ብዙሀን ያለቁበት ገደል አጥር ሳይታጠር መቅረቱ ግልጽ የተቀነባበረ ሴራ ማስፈጸሚያ ነዉ፤፤ለማነጻጸር ያህል የ2009 በዓል ዝግጅት ከሌሎች ጊዜያት የተሻለ ነበረ፤፤ የመሰብሰብያ ሜዳና ወደ ሀይቁ የሚወስደዉ መንገድ ለዘመናት አቧራማ የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት ግን ኮብል ስቶን ተነጥፎለታል፤፤ በተጨማሪም የገዳ አባቶችና ክቡራን እንግዶች የሚቀመጡበትም መድረክ በጥሩ ሁኔታ ተሰርተዋል፤፤ እሾሀማ አደናቃፊና የሰዎችን ዝዉዉር ይገቱ የነበሩት ዛፎች ተመንጥረዋል፤፤

2. ወታደራዊ ዝግጅቱ 1፡ መንግሰት ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ የታጠቁ ወታደሮችን በከተማዉ በሙሉና በብዛት ሀይቁ አካባቢ ከማስፈሩም በላይ ግድያዉ ከመጀመሩ ከሁለት ሰዓታት በፊት ጀምሮ (ጧት 1፡30) ተዋጊ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች እንዲያንዣብቡ ማድረጉ አንዱ ማሳያ ነዉ፤፤ ሀገራችን ዉስጥ እንዲህ አይነት ዝግጂት የሚካሄደዉ በጦርነት ጊዜ ነበር፤፤ ሌሎች ተመሳሳይ በዓላት ማለትም ህዝበ ክርሰቲያኑም ሆነ ህዝበ ሙስሊሙ በተለያዩ ቦታዎች ለአምልኮ ሲወጡ አሊያም መንግስት ራሱ የሚጠራዉ ሕዝባዊ ሰልፍ በሚካሄዱበት እንዲህ አይነት ዝግጅት ታይቶ አይታወቅም፤፤ በመሆኑም ዝግጅቱ የተቀነባበረ የግድያ ሴራ ነበር ማለት ነዉ፤፤

3. ወታደራዊ ዝግጅቱ 2፡ ጦር ሰራዊቱ ባልተለመደ ሁኔታና ለጦርነት ጋባዥ በሆነ መልኩ አካባቢዉን ቀደም ብለዉ ጦር አዉድማ አስመስለዉት ነበር፤፤ ከ200 kg በታች ድንጋይ የማይበሳቸዉ ድፍን ወታደራዊ መኪኖች ከላያቸዉ ላይ ስናይፐርና ፊታቸዉን የሸፈኑ ወታደሮች፡ እንዲሁም ከባድ መትረየችን ከረዣዥም የጥይት ሰንሰለቶች ጋር የተጠመደባቸዉ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎቸ በየቦታዉ ሐይቁ አካባቢ መኮልኮላቸዉ ሀቅ ነዉ፤፤ ይሄ ድርጊታቸዉ ህዝቡን ለመጠበቅ ነበር እንዳይባል ዉጤቱ ተቃራኒ ነበር፤ ጉዳት ከደረሰ በኋላም ያንን አላደረጉም፤፤ የዉጭ ወራሪም አያሰጋም ነበር፤፤ አላማዉ ህዝቡን ለማጥቃት ነበር፤፤ ከሎጂኩም በተጨማሪ የአይን እማኞችና ቪዲዮዋች ይሄን በሚገባ አሳይተዋል፤፤

4. የአጋዚ ጦር በአካባቢዉ መስፈር፡ ይህ ጦር ባለፉት 11 ወራት በመላ ሀገሪቱ ብዙ መቶዎችን የገደለና የኢትዮጲያዉያን ጠላት ተደርጎ የሚታይ ልዩ መቺ ሀይል ነዉ፤፤ ወያኔ በኢሬቻ እለትም በኦሮሚያ ፖሊስ ዩኒፎርም ሀይቁ አካባቢ ያሰፈረችዉ የአጋዚ ጦርን ነበር፤፤ እንደ አይን ምስክሮች ዪኒፎርሙን የቀየሩት ከዱከም ወደ ቢሾፍቱ መግቢያ አካባቢ በሚገኝ ስፍራ ነዉ፤፤ በእርግጥ የኦሮሚያ ፖሊሶችም ስፍራዉ ላይ የነበሩ ቢሆንም በቀላሉ መለየት ይቻል ነበር፤፤ አጋዚዎቹ በወታደራዊ ስነምግባራቸዉ (የተቆጡ፤ ተጠራጣሪና ከህዝብ ጋር መቀላቀል የሚከብዳቸዉ)፤ ሰዉነታቸዉ ፈርጠም ያለ፡ እያንዳንዳቸዉ በነፍስ ወከፍ የታጠቁና፤ ኦሮሚፋ የማይችሉ ነበሩ፤፤ የኦሮሚያዋቹ ቀለልና ትክዝ ያሉ ከህዝብ ጋር ቅርብ የሆኑ፡ ቀጠን ያሉ፡ ለአምስት ሆነዉ አንድ ክላሽና አራት ዱላ የያዙ፤ እንዲሁም ኦሮሚፋ የሚችሉ ነበሩ፤፤ ጥያቄዉ ለምን አጋዚ የሚል ሲሆን መልሱም የአጋዚ መቺ ሀይል በመሆኑ የመጣበት ተልእኮም መምታት ብቻ ነበር፤፤ ያንንም አሳክቶ ሄዷል፤፤

5. የሎጂስቲክ ዝግጅቱ፡ የዚህ ማሳያ የአጋዚ ወታደሮች ኬሚካል የተቀባ የጭስ ቦምብ መከላከያ መያዛቸዉ ሲሆን ጥቃቱን ሳይሰነዝሩ ይህንኑ ጨርቅ ኬሚካል እየቀቡ ለኦሮሚያ ፖሊሶችም እዛዉ ሆነዉ ሲያድሉ ታይተዋል፤፤ አንድ የኦሮሚያ ፖሊስም ይህን ጨርቅ ቦንቡ ሲተኮስ ለአንዱ ተጎጂ ቦታዉ ላይ ሰጥቷል፤፤ እዚህ ላይ ባይኔ እንዳየሁት ትክክለኛዉ የኦሮሞ አባ ገዳ ባያና ሳምባቶ መድረክ አካባቢ በቦምቡ ተጎድተዉ ሲያጣጥሩና በሁለት ሴቶች ተደግፈዉ ቆመዉ የነበረ ሲሆን እዛዉ አካባቢ የነበሩ የወያኔ ተሽዋሚዎቹ ምንም አልተጎዱም ነበር፤፤

6. የአባ ገዳ ቅሌት፡ ይሄም የቅድመ ዝግጅቱ አካል ነዉ፤፤ ከኦሮሞ ባሕልን በሚፃረር ሁኔታ tplf/opdo ደጋፊ ሽማግሌዎቻቸዉን ሰብስበዉ እንደ አባ ገዳ የሰየሙ ሲሆን እነዚሁ ቡችሎቻቸዉ በሐይቁም ቡራኬ በመድረክ ላይም ንግግር እንዲያረጉ መሞከራቸዉ፤ የተቀናጀ ዝግጅታቸዉን የሚያመላክት ሲሆን ተቃዉሞም እንዲነሳ ህዝቡን አነሳስቷል፤፤ ይሄ ድርጊት ነዉ እንግዲህ ወደ አሰቃቂዉ እልቂት የወሰደዉ፤፤ በሌላ በኩል ደግሞ ትክክለኛዉ አባ ገዳ በተለያዩ ምክንያቶች (ለዉጪ ሚዲያዎች ቃለምልልስ በማድረጋቸዉ፤ ወያኔ ወደ ኢሬቻ ለመሄድ ተመዝገቡ ሩጫም አካሂዱ ያለዉን በመቃወማቸዉ፤ ግድያዎችን በማዉገዛቸዉ፡ የተሳሳተዉ የOPDO-ኦሮሚያ ባንዲራ በመቃወማቸዉና ከአማራ ልኡካን ጋር ተገናኝተዉ በመተባበራቸዉ) ከወያኔ ጋር በመቃቃራቸዉ በስርዓቱና በሰዓቱ ወደ ሐይቁ እንዳይሄዱ የደረጉበት ምክንያትም የኦሮሞን ህዝብ መናቅ ሲሆን የሴራዉም አካል ነበር፤፤

7. ቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶች፡ ባልተለመደ ሁኔታ ከወያኔ ጋር በመረጃ የሚሰሩት የምናቃቸዉ የኦሮሞ ልጆች የዘንድሮዉን ኢሬቻ አልተሳተፉም ነበር፤፤ እነዚሁ ሰዎች በጣም የሚቀርቧቸዉን ሰዎች እንዳይሄዱ ሲጎተጉቱ የነበረ ሲሆን፤ ከጭፍጨፋዉ በኋላ ሰዉ ባለበት ሰዉ እንደሚያልቅ ”አንተ ታቅ ነበር፤”አንተም ታቅ ነበር” ተባብለዉ ሲጣሉ ነበር፤፤ OPDOም አደራጅቶ ለበዐሉ ያመጣተዉን ሰዎች በጊዜ ከሀይቁ አካባቢ አርቋቸዉ ነበር፤፤ በተጨማሪም የቀኑ እለት ብዙ ዉስጥ አዋቂዎች ከ3፡30 በኋላ ወደ ወንዙ አትሂዱ ሲሉ እንደነበር ብዙዎች ይናገራሉ፤፤ ይሄ ሁሉ መድረሻዉ የታቀደ አደጋ እንደነበር ማሳያዎች ናቸዉ፤፤

8. የOPDO ከፍተኛ ባለስልጣን/ሚኒስትር ማስጠንቀቂያ፡ ከቁጥር 7 ጋር በተያያዘ እኔ ባለሁበት ከኢሬቻ በዐል ሶስት ቀን ቀደም ብሎ ከመረጃ መረብ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለዉ የOPDO ከፍተኛ ባለስልጣን ከበታቾቹ ጋር ባደረገዉ ስብሰባ በተደጋጋሚ “ሰዉ መሞት የለበትም፤፤” “አንድም ሰዉ ሲሞት ሊያሳዝነን ይገባል፤፤” “መንግስት መተቸት አለበት፤፤ ያም በዕዉቀት መሆን አለበት፤፤” “ግን በሶሻል ሚዲያዉ አይነት መሆን የለበትም፤፤ ሶሻል ሚዲያ ተዉ፤፤” እያለ የምሬት ንግግር አድርጓል፤፤ የንግግሩም ፍፌ ነገር ምናልባትም የኢሬቻን እልቂት ሴራ ቀደም ብሎ ሰምቶ ማስጠንቀቂያ ማድረግ ይመስላል፤፤ ይህ ሰዉ በዛኑ ቀን በኢህአዴግ ተገምግሞ ከመጣ በኋላ ነበር የሄን ከወቅቱ አጀንዳ ጋር የማይገናኝ ነገር ይናገር የነበረዉ፡፡ ያ ሰዉ ዛሬ የሀገሪቱ ‘ጠቅላይ’ ሚኒስትር ሆኗል፡፡ እኔም እስከዛሬ ድረስ ዶ/ር አብይ ስለግድያዉ ቀደም ብሎ ሳያቅ አይቀርም ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡ ያኔ ንግግሩን በአካል ስለሰማሁ ምስክር ነኝ::

9. የጥቃቱ ታይሚንግ፡ ጥቃት ሰንዛሪ ሄሊኮፕተር አንድ ቦታ/ሀይቁ አካባቢ ማንዣበብ፤፤ አብዛኛዉ የበዐሉ ታዳሚዎች ከቦታቸዉ ሳይንቀሳቀስ ተቃዉሞአቸዉን ያሰሙ የነበረ ቢሆንም የጥቂት ቄሮዎች ወደ መድረኩ መሄድ፡ ባንዲራ የያዙና ጠንከር ያለ ተቃዉሞ የሚያሰሙ ወጣቶች ገደሉ አካባቢ መድረስ፡ የሄሊኮፕተሩ ደርሶ መተኮስና፤ ከመድረኩ ጀርባ ጫካ ዉስጥ የነበሩ ብዙ ወታደሮች ወጥተዉ ጥቃት መጀመራቸዉ ግጥምጥሞሽ ሳይሆን በጦር ሜዳ የሚካሄድ የማጥቃት ጥበብ ነዉ፤፤

10. ታርጌቱ፡ በተጨማሪም ገደሉ አካባቢ የተለያዩና ብዙ ሰዎች ሲፈራረቁበት የነበረ ሲሆን ጥቃቱ የተፈጸመዉ ግን ከሁሉም በላይ ጠንከራ ተቃዉሞ የሚያሰሙ ወጣቶች ባንዲራ ይዘዉ ከሀይቁ ወደላይ መተዉ ገደሉ ጋር ደርሰዉ ብዙም ሳይቆዩ ነበር፤፤ ይሄም ‘በወታደራዊ ጥበብ’ ትርጉም መሪ የተባሉትን ወጣቶች ለይቶ መግደያ ቀጠና ሲገቡ መምታት ይባላል፤፤ ለዚህ ተጨማሪ ማሳያ መሆን የሚችለዉ፤ ከጥቃቱ በኋላ ከተማ ዉስጥ ተሰብስበዉ ጠንካራ ተቃዉሞ ሲያሰሙ የነበሩትን ወጣት ወንዶችን ወታደሮቹ እያሳደዱ አስለቃሽ ቦምብና ክላሽ ይተኩሱባቸዉ ነበሩ፤፤ በሌላ አባባል ታርጌት ለይተዉ ሲገድሉ ነበር ማለት ነዉ፤፤

11. ወታደራዊ የጥቃት ጥንቃቄዉ፡ ታርጌት የተደረጉት ከሞት እንዳያመልጡ ጥንቃቄ ተወስዷል፤፤ በወታደራዊ ጥበብ ተዘጋጅተህ ጠላትን በደፈጣ ስታጠቃ ዋና ማምለጫዉን በጥበብ በመዝጋት ሲሆን ወደ ሌላኛዉ ቀሪ ማምለጫም ሲጠጋም ይህን ቦታ በወታደራዊ ሀይል መግደያ ቀጠና ታደርጋለህ፤፤ በቢሾፍቱም የሆነዉ ይሔዉ ነዉ፤፤ በወቅቱ ወደ ወንዙ የሚወስደዉ ደቡባዊ ክፍል ብቸኛዉ ነጻ ቦታ ና ቁልቁለታማ ሲሆን ታችኛዉ ክፍሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መያዝ ይችል ነበር፤፤ ወያኔዎች የመጀመሪያ ቦምብ የተኮሱት ህዝቡና ይሄ ቦታ መሐል በመሆኑ ሰዎች ወደዛ መሸሽ አልቻሉም፤፤ በተጨማሪም ወታደሮቹ ብዙ ሆነዉ ወደዚ ቦታ መተዉ ይጠብቁ ስለነበር አንድም ሰዉ ወደዚህ ሊሸሽ አልቻለም፤፤ ምዕራባዊ ክፍሉ ወደ መድረኩ የሚወስድና ብዙ ወታደሮች የሰፈሩበት ነበርና ወደዛ መሸሽ አይታሰብም፤፤ ምስራቃዊ ክፍሉ ገደል ነዉ፤፤ ብቸኛዉ የመሸሻ አቅጣጫ ወደ ሰሜን ነበር፤፤ ችግሩ ግን በዚህ ቦታ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ተጨናንቀዉ የሰፈሩበት በመሆኑ፤ እንዲሁም የወያኔ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎችና እግረኛ ወታደሮችም ከሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ሆነዉ ወደ ህዝቡ (ሰሜን) ሲተኩሱ ስለነበር ሰዉ መሸሻ አጥቶ ከፍተኛ ጋጋታ የተፈጠረ ሲሆን ብዙዎቹ የምንወዳቸዉና የሚወዱን ኩሩና ነፃነት ናፋቂ ወገኖቻችንን ተገፍተዉና ተመተዉ ወደ ገደሉ ገብተዉ እንዲያልቁ ተደርገዋል፤፤

12. ከበዓሉ በፊትና በኋላ ግድያዉ መቀጠሉ፡ ሌላዉና አንዱ ቁልፍ ጉዳይ የወያኔ ሰራዊት ለወራት በዘለቀዉ የ#OromoProtests ምክኒያት ብዙ መቶዎችን የገደለ መሆኑንና ከ #IrreechaMassacre በኋላም ግድያዉ መቀጠሉ የኢሬቻ እለት ህልፈቶችም የዚዉ አካል እንደሆነ ማሳያ ነዉ፤፤ ህዝብና ወያኔ በተቃቃረ ሁኔታ ዉስጥ ሆነዉ፤ ወያኔም ከበዓሉ በፊትና ከበዓሉ በኋላ ምንም የተለየ አካሄድ፤ ፖሊሲና አቋም በተጨባጭም ያላሳየ በመሆኑ የበዓሉ እለትም ያዉ ገዳዩ እራሱ እንደነበር በምክንያታዊነት መግለጽ ይቻላል፤፤

13. የዛኑ እለት የቀጠለ ግድያ፡ በገደሉ ዉስጥ ሰዎችን ከፈጁ በኋላም በቢሾፍቱ መሐል ከተማ ሰርክል አካባቢ በታጨቀዉ ህዝብ ላይ መጀመሪያ ጭስ ቦምብ በመተኮስ ተሰብሳቢዉ ወደ ተለያየ አቅጣጫ መሮጥና መራወጥ ሲጀምር፡ በዛ ግርግር በመጠቀም ቢያንስ ስድስት ታርጌት የተደረጉ ወጣቶች በጥይት ተመተዉ ተገለዋል፡፡

14. ወቅቱንና ቦታዉን ያላገናዘበ እንቅስቃሴ፡ ህዝብና መንግስት ሆድና ጀርባ በሆነበት፤ ሚሊዮኖች በአንድ ጠባብ አካባቢ በተገኙበት፤ እንዲሁም ከህፃን እስካዋቂ እዚህ መሀል በተገኘበትና፤ ይሄ ሁሉ ሰራዊትና በሄሊኮፕተር የተደገፈ ከባድ መሳሪያዎች ባለበት ሁኔታ ተኩስ ማሰማት ምን አይነት ዉጤት እንደሚያመጣ ማንም ማሰብ የሚችል መገንዘብ ይችላል፤፤ በዚህ ሁኔታ ጭስ ቦምብ ብቻ መተኮስ ራሱ ሰዎች ከተተኮሰበት ቦታ እንዲርቁ የሚያደርግ ስለሆነ (ገደልም ባይኖር) ሲንቀሳቀሱ ተረጋግጠዉ መገዳደላቸዉ አይቀሬ ነዉ፤፤ በመሆኑም እዛ ቦታ ላይ-ገደልም መኖሩ እያወቁ-ጥይት መተኮስ እያወቁ/አቅደዉ ተሰብሳቢዎቹን ወደ ሞት መላክ ብቻ ነዉ የሚል ትርጉም ይኖረዋል፤፤

15. የሰላዮች ማሰጠንቀቂያ፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከእልቂቱ በኋላ ሲቪል የለበሱ የወያኔ ሰላዮች ቪዲዮ የሚቀርጹና ፎቶ የሚያስነሱ ሰዎች ድርጊታቸዉን እንዲያቆሙ ሲያስጠነቅቁ ነበር፤፤ የዚህ ዋና ምክንያት ሟቾች በቦምብና በተለይ ደግሞ በጥይት መገደላቸዉን ለመደበቅ ሲሆን ወታደራዊ እንቅስቃሴዉም በአደባባይ እንዳይታይባቸዉ ነበር፤፤

16. የንብ መንጋ፡ እኔም ባለሁበት ግድያዉ ከተፈጸመ ከሁለት ደቂቃ በኋላ ለተጎጂዎች እርዳታ ለማድረግ እንደገና የግድያዉ ቦታ ተሰብስበን ነበር፡፡ በዚህም ብዙ ከሞት የተረፉትን ተንከባክበንም አነጋግረንም ነበር፡፡ ሆኖም ወያኔዎቹ (ካምፓቸዉ በደቡበ ምስራቅ የመግደያ ጉድጓን ያዋስናል) እኛን ለመበተን ሌላም ዘዴ አዘጋጅተዉ ነበር፡፡ ይሆም አደገኛ ተናዳፊ የንብ መንጋ ሲበትኑብን ሰዉ እንዳለ ተበተነ፡፡ ይሄም ሌላኛዉ የዝግጅቱ አካል ነበር፡፡

ማስታወሻ፡ የዚህ ፖስት ጸሀፊ በወቅቱ ቦታዉ ላይ የነበረና የአይን እማኝ ሲሆን ተጨማሪ ደጋፊ መረጃዎችንም ከቪዲዮዎችና እዛዉ ቢሾፍቱ ከተማ በመቆየት ሰብስቦ አጠናክሯል፤፤ ለመረጃዉ እዉነትነትም እምነቱን የሚሰጥ ሲሆን የህሊና ፍርድም ይቀበላል፤፤ በተጨማሪም አባ ገዳ ባያና ሰንባቶ በወቅቱ በቦምቡ ተጎድተዉ እርዳታ ሳይደረግላቸዉ መቆም አቅቷቸዉ በሁለት ሴቶች ተደግፈዉ ለመቆም ሲሞክሩና ዉሃ ላያቸዉ ላይ ሲፈስ አይቷል፡፡ በወቅቱ ካድሬዎቹ ና የኦህዴድ ምልምል አባ ገዳ ነን ባዮችም መድረክ ላይ ቁጭ ብለዉ ግድያዉን ሙሉ ለሙሉ ሲያዩ ነበር፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s