Melkamu Temesgen: #የነ ሳሞራ ጦር ዳር ድንበር “በወታደራዊ ይለፍ ቃሉ” ምሽጉ ኮሌጅና ዩኒቬርስቲ ነው፤

#የነ ሳሞራ ጦር ዳር ድንበር “በወታደራዊ ይለፍ ቃሉ” ምሽጉ ኮሌጅና ዩኒቬርስቲ  ነው፤

Melkamu Temesgen (via Facebook)

ህወሃት እና የወያኔ ጦር፣ኦሮሞን አያምኑም፣አማራን ሆኔ ሲዳማንው አያምኑም፣ከጂግጂጋና  ከመቀሌ ካልሆኔ የክልል ፖሊሲን፣የክልል ፍርድ ቤቱን፣አቃቤ ህጉንም ሆኔ ዳኛውን አያምኑም ። የክልል ፍርድ ቤቶች በህገ መንግሥትና በአዋጅ የተደነገገ “ሥልጣን አላቸው “ይባላል እንጅ “በህወሃት የተከሰሰው ሰው “የትግሬ ደኛ በጉዳዩ በመግባት ተጽዕኖ መፈጠር ወደሚችልበት ፌዴራል ፍ/ቤት ክሱ መመራቱ

የግዴታ ነው።በህወሃት የሚከሰሱ ሰዎች ሁሌም “ወንጀላቸው” ተመሳሳይ ሲሆን የሚጠቀስቸባውም የወንጀል

አንቀጽ ተመሳሳይ ነው።”ሽብርተኝነትና ህገ መንግሥታዊ

ሥርአቱን በኃይል መጣል”  የሚለው ሁሉም ተከሳሾች

የሚቀርብ ክስ ነው።ሰው የገደለ፣ሌባ ፤የዘረፈ፣

ንብረት የቀማ፣አለአግባብ ሥልጣኑን የተጠቀመ፣ሰርቆና

ዘርፎ ፎቅ የሰራ፣ህዝብን በአደባባይ የረሸነ በህወሃት አይከሰስም። የጥቃት ጉዳቶች ሰለባ ነኝ የሚል ህዝብም

ክስ ማቅረብ ቀርቶ “አስቦትም” ከሆኔ እራሱ ሽብርተኛ ነው።መንግሥት ያሰማራው  ጦር  ፣650ሺህ ህዝብ ስያፈናቀል ፣የተጎዳውን ህዝብ መልሶ እያጠቃ፣ህዝብን

የወረረውን ታጣቂ ኃይል በሎጂስቲክ፣ በትጥቅ፣በስልጠናና

በስምሪት ድጋፍ የሚሰጥን የመንግሥት ጦር አዛዥ ጄኔራል አብራሃ መክሰስ “ንጉስን መክሰስ”ነው።

 “ንጉሥ አይከሰስም”…የትግራይ ጄኔራሎችና የህወሃት አለቆችም “ንጉሶች” ስለሆኑ ጨፍጭፈውና ረሽነው፣ ገድለው አስገድለው “የሀገር ባላውለታነታቸው” ይዘከረል።
ህወሃትና ጦሩ ዩኒቬርሲቲና ኮሌጆችን አያምኑም፣ጄኔራል

ሳሞራ “…በችሎታቸው ከዩኒቬርስቲዎች  የዶክትሬት ዲግሪ

የተሸለሙ፣ለሸለማቸው ተቋም ቢያንስ ወገናዊ መሆን ሲገባቸው…” የዩኒቬርሲቲ ስም እንድነሳባቸው አይፈልጉም ።

ሰሞራ አንደ ተናገሩ እንደተባለው “…ከአሥር ዲግሪ አንድ

ጠመንጃ..”ብለዋል ይባላል። ዛሬ በሀገሪቱ ዩኒቬርስቲ

 ውስጥ ያሉት የኦሮሞ፣የአማራ፣የሲዳማም ሆኔ የሌላው

ብሔር ተወላጆች በነጻነት መማር ይፈልጋሉ፤

በነዚህ ዩኒቨርስቲዎች የነ የስብሃት ነጋና የዘመዶቹ ልጆች፣ የአባይ ፀሃዬ፣ የስዩም መስፍን፣ የአርከበ ዕቁባይ፣ የፀጋዬ በርሔ ፣የብርሃኔ ገ/ክርስቶስ፣የሳሞራ የኑስ፣ የጌታቸው አሰፋና የሌሎችም ዘራፊ ወያኔ ልጆች የሉም። እነሱ አባቶቻቸውን ተክተው ልጆቻችንን ሊገዙ በቻይናና በምዕራቡ ዓለም ትልልቅ ትምህርት ቤቶች በተዘረፈ የህዝብ ሃብት ይማራሉ።በሀገራቸው በአጋዚ የሚገደሉት ግን የምስክኑ ህዝብ ልጆች ናቸው።ልጆቹ ከሞት ወደሚያመልጡበት 

 ሌላ ሀገር ሊልካቸው አቅሙን ከየት ያምጣው?ያለውንም ተቀምቷል።የእርሻ ማሳውን ፣የንግድ ቤቱን የሥራ ፈቃዱን

ተነጥቋል። ከውጪ ንግድ፣ ከሥራ ጨረታዎች፣ከባንክ

አገልግሎት እየተገፋ ያለው ህዝብ፣ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው የወህሃት አባላት ጥያቄ በተሟላ ከተመለሰ 

ቦኋላ ነው።ይህ ጉዳይ ያላማረረው ኦሮሞ የለም።

አማራውም በህዝብነቱ ይህ ጉዳት ደርሶበታል። 

የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆናችሁ ፣እንደ እናንተ ባሉ ምስኪን በሆኑ በማናቸውም ብሔር ተወላጅ ላይ እጃችሁን አታንሱ! 

በትምህርት ተቋሞች ውስጥ፣ስውር ትጥቅ ይዞ ለአጋዚ እየሰለለ የሚያስገድላችሁን ግን ትምህርት ላይ ሳይሆን ድርጅታዊ ስምሪት ላይ መሆኑን  አትዘንጉት!

በሀገራችሁ ተምራችሁ ሰው የመሆን፣እራሳችሁን በመቻል

ለፍቶ ከሳደጋችሁ ወላጅ ትክሻ ወርዳችሁ፣  ሌላው ቢቀር  እናት አባቶቻችሁ “እሴይ ተመስገን” ብለው ትንሽ የህሊና ዕረፍት እንዳያገኙ ተስፋችሁን ያጨለመው የወያኔ ዘረኛ ስርዓት ነው። የህወሃት ሥርዓት እንዲያበቃለት ደግሞ  የሚደረገው ትግል አቅጣጫው እንዳይቀይር መልሶ በወያኔ በሚዘጋጅ ወጥምድ ውስጥ እንዳይገባ ጥንቃቄ ይፈልጋል።

የዩኒቬርሲቲ ተማሪም ይሁን ህዝቡ የህወሃትን የተንኮል

መረብ በጥሶ ማለፍ ይኖርበታል።።ወያኔዎች የራሳቸውን ወገኖች እየገደሉ “ደርግ ገደላቸው ” ብለው በማስወራት ድጋፍ ያሰባሰቡበት አጋጣሚ ብዙ እንደ ነበረ፣አብሮአቸው የነበሩ እነ አብራሃም ያዬህ እነ አረጋዊ በርሔ የገለጹባትን ጊዜያት አስታውሳሌሁ።።

ስለዚህ ዛሬ በዘረፋ በከማቹት ሀብት፣በመንግሥት መዋቅር ውሰጥ  ህወሃት ብቻ በሚገለገልበትና በሚጠቀምበት መከላከያና ደህንነት ተቋሞች አቀነባባሪነት፣እጅግ የረቀቀ

ወጥመድ እንደሚያዘጋጁ አለመዘንጋት ነው።
ይህንን በሚከተለው መልክ ለመፈጸም ይሞክሩ ይሆናል፣
1ኛ/የራሳቸውን ሰዎች ገድለውና አስገለድው፣ኦሮሞ ወይም

አማራ እንደፈጸመው አድርጎ በማቅረብ ወደ ኋላ የማይሉ

ጨካኞች እንደሆኑ መረዳት ተገቢ ነው፣  ከዓመታት በፍት

ፍንፍኔ ትግራይ ሆቴል ውሰጥ ቦንብ አፈንድተው ፣”ጥፋቱን

የፈፀሙት የኦነግ አባላት ናቸው” ብለው ያነ ባሰሯቸው የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ባለፈው ጊዜ የሞትና የዕድሜ

ልክ ፍርድ ቅጣት መወሰናቸውን አይተናል።

2ኛ/ የራሳቸውን  ሰዎች በመገፋፋት፣..”እኛ አለንላችሁ” በማለት ህዝብን በዕልህ ውስጥ በሚከቱ ድርጊቶች፣

በንዴትና በብስጭት ሰዎች ተነሳስተው ስሜታዊ ዕርምጃ እንዲወስዱ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የሚሸረቡ ዘዴዎች፣ይህ በተቃራኒያቸው የቆሙትን ሰዎች ከሥራ ለማባረር፣ለመስከሰስና አበሳጭቶ ለማራቅ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው።

3/እንደተለመደው በዕምነት፣በባህልና በማንነት  ላይ 

በተመሠረተ የተሸነባበረ ተንኮል ህዝብን ወደ ስሜታዊ የበቀል ድርጊት የሚመራ ትንኮሳ በማዘጋጀት ኦሮሞና አማራውን ማጋጨት፣ክርስቲያንና ሙስሊሙን ማቃቃር፣

ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው ከዚህ ቀደም በጂማ ዞን ቅዱስ ቁራንን በመቅደድ ነውሪ በሆኔ መንገድ በተማሪዎች

መጸዳጃ ሽንት ቤቶች ውሰጥ በመጣል ክርስቲያኖች እንደፈፀሙት አስመስሎ በማቅረብ ግጭት እንዲፈጠር

 የተጠቀሙበት ነው።

በኦሮሞ ፕሮቴስት በአርሲና በአንዳንድ አካባቢዎች

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በማቃጠልና በማዘረፍ

ኦሮሞዎች አማራን ለማጥቃት እንዳደረጉ ለማረቅብ

እንደሞከሩ የሚወታስ ነው።

4ኛ/ በታሪክ ፣ በማበህራዊ ህይወትና በህዝብ ልማዶች ውስጥ ያሉትንና እያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ “..የኔ ነው..”

የሚላቸውን ወጎች በተቀነባበረ ዘዴ በማንቋሸሽ በኃለቀርነት ወይም በአሰነዋሪነት ተርጉሞ ግጭትንና አለመግባባትን

እንዲጋብዝ ማድረግ፤ያንንም ለምሳሌ ኦሮሞው “በፀረ አማራነት፣በፀረ ጉራጌነት ” አማራው “በፀረ ኦሮሞነት፣በፀረ

ሲዳማነት” እንዳደረገው ለቀቅረብ እንደሚችሉ ነው።

5ኛ/ ህዝብ ይወዳቸዋል የሚባሉትን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን፣አክትቭስቶች፣የኪነ ጥበብ ሰዎችን፣የሃይማኖት መሪዎችንና በግላቸው ህዝብ ውስጥ ተወዳጅነት ያላቸውን ግለሰቦች በሚመለከት ፣ስድብና ስም መጥፋት በታከሉባቸው ሥዕሎችና ካርቱን፣በበራሪ ወረቀት፣በግርግዳ ግራፍክ፤በዜማ ፣በስፖርትና በመዝናኛ ቦታዎች፣በሌሎችም ዘዴዎች በአጻያፊና አስነዋሪ ቃላት እንዲሰደቡ በማድረግ ወጣቶች እንዲጣሉና ነገሩ የብሔር መልክ እንዲይዝ ሁኔታዎችን ማመቻቸት የተለመዱ የወያኔ ሰላዮች ሴራ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

ለዚህ  ምሳሌ በአንድ ወቅት በክልሎች የስፖርት ውድድር ባህር ዳር ላይ “አማራ ወጣቶች የኦሮሞን ህዝብ ክብር የሚነካ ስድብ ተሳድበዋል” ተብሎ የነበረ ሲሆን ከቆይታ ቦኃላ ነገሩ የተቀነባበረው ተመልመለው ከመከላከያና ከደህንነት በስቪል ተመልካችነት ወደ ስታዲዮሙ በተላኩ የደህንነትና የመረጃ ሠራተኞች እንደሆኔ ተገልጿል።በወቅቱ ተደረገ የተባላው ነገር የውድድሩን ተሳታፊ  ጨምሮ ብዙ  የኦሮሞ ተወላጆች ማስቆጣቱን አውቃሌሁ።ስለዚህ ህወሃት ምክንያት ፈጥሮ ጦሩን በህዝብ ላይ ለማሰማራትና ለመግደል ፣ህዝቡ ተቃቅሮ ትኩረቱ እንዲቀየርና የነሱን ግድያና ዘረፋ ዘንግቶ  ወደ ሌላ አጀንዳ እንዲሸጋገር የሚፈፀመውን ሸርና ተንኮል በሚገባ መጠንቀቅ ያሻል።ህወሃት “መከላከያና ፌዴራል ፖሊሲን” 

የራሱ ብቻ ጦርና መመኪያ አድርጎ የማቅረቡ ማስረጃ

ከአዛዦቹ ጀምሮ እሰከ መስመር መኮንኖች በትግራይ ልጆች

የበላይነት መዋቀሩ ብቻ ሳይሆን፣ የህዝብ ተቃውሞ በወያኔ

ላይ ስበረታ ፣የህወሃት ጋዜጠኞችና አክትቪተቶች እነ ሚሚ ስብሃቱ እነ ዳንኤል ብርሃነና መሰሎቸቻው”ዱላና ክንድ

 ያስፈልጋል…መከላከያውና ፌዴራል ፖሊሲ ተልዕኮውን

እንዲወጣ አልተደረገም…ወታደራዊ መፈንቀለ መንግሥት ቢደረግ ይመረጣል…በኮንትሮባንድና በህገ ወጥ ንግድ ዝውውር የክልል ፖሊሶች ሳይሆኑ መከላከያው ሃላፊነት

መወሰድ አለበት…”እያሉ ስጽፉ መሰሎቻቸውን በዚህ ዙሪያ ለውይይት ስጋብዙ እየያን ነው። ዱላው እንዲያርፍበት፣ የሚዘረጋው ክንድ እንዲደቁሰዉ የተፈለገው የኦሮሞን 

ህዝብ ነው። ወታደራዊ መፈንቀለ መንግሥቱ የሚፈለገው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የትግሬ ጄኔራሎች ኦሮሚያን በስምንት ቀጠናዎች ከፍለው ሲገዙ የትግራይ ባለሃብቶች   ወደ ” ንብረቶቻቸው ” ሲሄዱ በወታደር ታጅበው በኩራትና

በንቀት ህዝቡን እየገለመጡ ስያልፉ፣የፈለጉትን ዘርፈውና ጭነው ስወስዱ ትዝታ ስላላቸው ነው።የክልል ፖሊስን ሥራ ከህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ለማስወጣት ሀሳብ

የሚመነጨው ፣እነ ማንን ለመጥቀምና በነማን ላይ ለመዝመት እነደተፈለገም ማብራሪያ የሚፈልግ አይሆንም። 

ስለዚህ  ህወሃትን ለማንበርከክ መልሶ ህወሃት በዘዴ በሚያዘጋጃቸው ወጥመዶች ውሰጥ አለመግባት የወያኔን ዕድሜ እንደሚያሳጥረው መገንዘብ መቻል ተገቢ ነው።

ወያኔዎችና ቤተሰቦቻቸው በህልማቸው ይኖራል፣ ብለው ባለሰቡት ማሣ ውስጥ ገብተው የሚችሉትን ያህል

እየዘረፉ ነው።ይህንን ዘረፋ የተቃወመ በነሱ መንግሥት አሰራር ምህረት የሌውም። ለኦሮሞው እንዳይኖርባት የተከለከለው ኦጋዴን የተገደለበትና በግማሽ ሚሊዮን የሚቆጠረው የተፈናቀለባት ለህወሃት መኳንንትና ደረሶ ለኢትዮጵያና ለፌዴራሉ ሥርአት ጉዳይ ኮከብ ፕሮፖጋንዲስቲ

ሆኖ ለቀረበው ወመኔው አብዲ ዑመር ኦጋዴን የግላቸው ሆናለች።

 አማራው ከጠላት ለብዙ አመታት ለኖረበት ለመተማ፣

ለሽርቆሌ፣  ለፓዊ ባዕድ ሆኖ የአካባቢውን መኖር ሰምተው የማያውቀው የትግራይ ልጅ መሬቱንና ማዕድኑን ከአድዋ መጥቶ ይዘርፋል።

አሶሳ ለኦሮሞው ውጭ አገር ሆና ይፈናቀልባታል፤ ጋምቤላን አኝዋኩ ጠብቆ መቆየቱ ሃጢያት ሆኖበት 420 አኙዋክ በአንድ ቀን ተገድሎ የተረፈው ተባርሮ ዬት እንደገባ ሳይታወቅ የህወሃት ባለሥልጠናትና ዘመዶቻቸው በብቸኝነት  መሬቱን በኢንቬስተር ስም ነጥቀውታል። የህወሃት አባላት

የክልሉ ምክር ቤት አባላትም ናቸው። 

ኦሮሞ ተካፍለን አብረን አንበላም ያለበት ዘመን የለም።የህወሀት ሰዎችም ይህንን ያውቃሉ።ንፉግ ነውም አይሉትም…”ጠባብ” ብለው ግን በማይገባው ዘይቤ  ያሸማቅቁታል። ለወያኔና ለቤተሰቦቻቸው ትህትና

ያሰየና ስታገስ በብድሩ ያልተደፈረ ህዝብ የለም።

ከመደፈርና ከመዋረድም አልፎ ተገድሏል፣እየተገደለም

 ነው።
የኦሮሞ ቄሮዎች፣ የአማራ ፋኖዎች የጠየቁት “እናንተ ማን ናችሁ “ነው?.. ሌሎችን አስራችሁ፣ ገድላችሁና ከቄኤ አባራችሁ አገርና ህዝብን የምትዘርፉት ለምንድነው?”  ነው። በዚህም ሳያበቃ ለሶስት ዓመት በተካሄደው ህዝባዊ ትግል የተደናገጡትና የጌቶቻቸው አልጠግብ ባይነት ያሳሰባቸው፣ አገልጋይነታችውም የሰለቻቸው የኢህአዴግ አባላት የህዝባቸውን ሮሮ ከመስማት አልፈው ወያኔን እየተገዳደሩ ነው።

 ለህወሃት  ዘራፊቸች በኦሮምያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ ወዘተ እንደወትሮው መዝረፍ ይቅርና መንቀሳቀስም እየከበዳቸው መጥቷል ። የተያያዘው ዘመቻ “እንዴት አድርገን የቀራቸውን አሟጠን እንሂድ?” ነው።…”እንዴት አድርገን አብረን መኖር እንችላሌን ?” ያሉበት አንድም ቀን የለም።ዛሬ ጄኔራሎቻቸው፣ኮሎኔልና ሻላቃው ኮንትሮባንዲስት ነው። የህግና የጦር ደጀን ድጋፍ ታክሎበት መንግሥት ያስታጠቃቸው ኃይሎች፣ባንዲራ እያዉለበለቡ በመንግሥት

ተሽከርካሪ ኮንትሮባንድ ያመላልሳሉ፣ህግ አስከባሪውን አስፈራርቶ ለማለፍ፣የተደረደረላቸውን ኮከብ በአመልካች ጣት እያሳዩት ኬላ ሰብረው ይሄዳሉ።

የማንነታቸው መግለጫ መታወቂያና ለጫኑት ዕቃ የተፈቀደበትን ማረጋገጫ ስጠየቁ ሽጉጥ ይመዛሉ።ይተኩሳሉ፣የተለመደውን መከላከያ ያዛሉ፣”..ጠባቦች ወይም ትምክህተኞቹን” ያሳፍሳሉ፣

ያሳስራሉ፣ ለበቀሉም እንደ ጨለንቆ ያላአንዳች ጥፋት

ንጹህ ወገኖቻችን በሀገራቸው፣በቄአቸው፣በገዛ ማሣቸው ላይ ይረሽናሉ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s