ሞቲ ቢያ: ስለራሳችሁ  ብላችሁ  መልስ ስጡን!! 

ስለራሳችሁ  ብላችሁ  መልስ ስጡን!! 

ሞቲ ቢያ

እ.ኤ.አ በ1996፣ የዛሬ ሃያ ዓመት አንድ የአፋር ወጣት ለደርግ ወታደሮች፣ “መጣችሁብኝ እንጂ አልመጣሁባችሁም” ያለውን ጠቅሼ በ”ኦሮሚያን በፈረቃ??” መጽሃፌ ላይ አውጥቼ በነበር። ዛሬም ተዋኒያኑ ተለወጡ እንጂ መድረኩና ጫወታው እንደዚያው እንደቀጠለ ነው። 

ለመሆኑ፣  ዛሬም   ሃጎስ ከጨለንቆ  ምን ይሠራል? የመከላከያ ሠራዊት ከዩኒቬርሲቲዎች ምን ይሠራል?? ለትምህርት የሄደን ተማሪ የሚያሸብር ጦር የትኛውን ሽብርተኛ መከላከሉ ነው?? 

ዜጋን ያለምንም ፍትህ መግደል ወንጀል ነው። እራሱ ሕግ ጥሶ፣ ነፍስ ገዳይ ሆኖ የትኛውን ሕግ ያስከብራል?? ሀገር መከላከያ ማለት ወደ ውስጥ ተመልሶ ዜጎችን በጠራራ ፀሃይ መረሸን የሆነው በየትኛው ሕግ ነው? ወገን ሕይወቱን የሚያጣው ስለየትኛው ወንጃሉ ነው? ጠብመንጃ መያዝ  ብቻ ሕግ፣ ዳኛና ቅጣት ፈፃሚ  ለመሆን ያስቻለው እንዴት ነው?  ስሙን እንኳን የማያውቁትን ሜዳ  ላይ    ባገኙት  በሰኮንዶች ጊዜ ውስጥ  ሞት እንደሚገባው ወስኖ በጥይት አረር ማቃጠሉ ምን የሚሉት የሀገር መከላከያነት ነው??

የትግራይ አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞችና እህቶች! እስቲ መልስ ስጡን!! ግዥዎቻችሁ ሕይወት እያጠፉ፣ ደምን እንደውኃ፣ እምባንም እንደጎርፍ  እያፈሰሱ እናንተን ሊወክሉ ይችላሉን?? በዚህ ክፉ ዘመን እንደናንተው ወላጆች የሆኑ የኦሮሚያና የአማራ አባቶችና እናቶች የተገድሉባቸውን ልጆቻቸውን በወጉ  እንዳይቀብሩ መከልከላቸው ለምንድን ነው??

ይህ እናንተን ከሚወክል አካል ይጠበቃልን?? ይህስ የጨዋው የትግራይ ሕዝብ ባህል ነውን?? ስለነገ ብላችሁ እስቲ መልስ ስጡን!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s