…..የሚመሩትን ህዝብ ..በእሳትና በጭድ….በጋኔንና አጋንንት እያስመሰሉ ሀገር የሚገዙ ደፋሮች፣

…..የሚመሩትን ህዝብ ..በእሳትና በጭድ….በጋኔንና አጋንንት እያስመሰሉ ሀገር የሚገዙ ደፋሮች፣

Melkamu Temesgen (via Face Book)

ከዛሚ ራዲዮ ጋር  ዴሰምበር 2/2017 በነበረው ቃለ ምልልስ የቀድሞው የወያኔ መንግሥት የኮሙኒከሸን ጉዳዮች ሃላፊ ሚንስቴር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚከተሉትን የፕሮፖጋንዳ ወሬዎች አሰምቶናል።

#….”ህዝብን ከድተናል “ብለን አምነናል፤

#…”ህወሃት የውሸት ሪፖርት ማስቀረት አለበት”

#…”አቅም ያለው ሰው እንደ ስጋት የሚቆጠርበት ሁኔታ መቅረት አለበት..”

#…የህወሃት ዴሞክራሲ እንደ ተፈሪ ሱሪ ከላይ ሰፊ ከታች። ጠባብ ነው..”

 በሚናገሩትና በሚያስተላልፉት መልዕክት የህዝብን ክብርና ታላቅነት አንቋሽሸው ለግል ጓደኛ እንኳን ለማለት በሚከብድ የወረደ ንግግር፣የሁሉም የበላዮችና ለሀገሪቱ የተለዩ ሰዎች እንደሆኑ የሚሰብኩ፣ ሰው በላዎች አሁንም መሪዎች ለመሆን ቅስቀሳ ጀምረዋል።

ጌታቸው ረዳ የመንግሥት ኮሙንኬሸን ጉዳዮች ሚንስቴር በነበረ ጊዜ ፣የኦሮሞን ህዝብ ተቃውሞ አስመልክቶ ሲሰጥ በነበረው መግለጫ “…ጋኔኖችና አጋንንቶች”ብሎ ሲሰደብ ይህን “መብት ” የሰጠው ፣የህግ የበላይነት አልነበረም።

እንደ ልቡ እንዲሳደብና ህዝብን እንዲያንቋሽሽ ልብ የሰጠው የህወሃት የበላይነት ነው።የአማራና የኦሮሞ ህዝብ “እሳትና ጭድ ነው ” ለማለት የተማመነው የህዋሃት የበላይነትን ነው።

እንደፈለገው ይሳደብ ዘንድ ልብ የሰጠው በመከላከያ ፣በደህንነት ፣በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ተቋማት ውሰጥ መስል ወገኖቹ ያላቸው የበላይነት ነው።የህግ የበላይነትማ ቢኖርማ ተጠያቂና ወንጀለኛ ነበር።

ዛሬ ” ህዝብን ከድተናል “ብለው “እንዲህ ብለናቸው እንሞክር ” የሚል ፕሮጄክት ይዘው ቀርበዋል።የከዳ ሰው ይዘርፋል፣ያፈናቅላል፣ይገድላል።ስለ ድርጅታቸው ገዳይነት እየደበቁ አሁንም ልዋሹን የሚሞክሩ ደፋሮች፣በቅድሚያ “እናገለግለዋለን” የሚሉትንና ስገድሉትና ስረሽኑት የነበረውን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው፣ህዝቡ ይቅር ስለማለቱ ማረጋገጫ የላቸውም። የዘረፏቸውን የህዝብ  ሀብቶች ህዝቡ በቁጭት እያየ ዝም ስል ለወዳጅነት ያቆያቸው ይመስላቸዋል።

 በተቀነባበሩ የሃሰት ወንጀሎች ያሰሯቸው፤የገረፏቸው አካላቸው የጎደለ፣ቤተሰባቸው የተበተነ፣የት እንደደረሱ ያልታወቁት ወገኖቻችን የነሱ “..የውሸት ሪፖርቶች” ሰለባ መሆናቸውንም ማመንና በድርጅታዊ መግለጫቸው መጥቀስ ነበረባቸው።

“አቅም ያለው ሰው እንደ ስጋት የሚቆጠርበት ሁኔታ መቅረት አለበት” ይለናል…ጌታቸው ረዳ፤….ለመሆኑ ህዝብን የሚሳደብ፣የሚያንቋሽሽና ተቃውሞን በመፍራት የህዝብ ወገኖችን በሽብርተኝነት እየፈረጀ በማሰር የቁም ስቃይ እያሳየ ያለው ኃይል…”አቅም ያለውን ሰው”እንደ ስጋት አይቆጥርም ለማለት ነው??? ማዕከላዊ፣ ቅልንጦ ፣ሸዋ ሮቢት፣ሁርሶ፣ጦላይ፣አዋሽ አርባ የተሰቃዩ የተገረፉና ለሞት የበቁት ስንት ናቸው????

ወያኔዎች በስጋት የቆጠሯአቸው  ጋዜጠኞች፣የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣በነሱ መስመር አንሰለፍም ያሉ የሃይማኖት ሰዎች(ድምጻችን ይሰማ) ነጻ ስለመሆናቸው ስያረጋግጡና ይቅርታ ስጠይቋቸው ነበር “..አለመፍራታቸውን” ህዝቡ የሚረጋገጥላቸው።

“አቅም ያለው ሰው እነደ ስጋት አይቆጠርም” ከተባለ የሽብር አዋጁ የህዝብ ብሶት ገላጮችን ለማፈን ባልዋለ ነበር፣ዛሬ ትምህርት ተቋሞች እሥር ቤቶች  ባልሆኑ ነበር፣ታንኮች ከተማ ውስጥ ባላጓሩ ነበር፣መትረዬስና አዳፍኔ የታጠቁ አጋዚዎች ያለ ርህራኼ ህፃናትን ከእናት ነጥለው ባልገደሉ ነበር።የአስቸኳይ ጊዜ በማሳወጅ ጠቅላላውን ህዝብ ግዞታኛ ባላደረጉ ነበር።

እነ ጌታቸው ረዳ ለስሙ በመንግሥት መዋቅር በቀጥታ የነበራቸው ተሳትፎ ተሽሮ እነሆ በኢህአዴግ ምክር ቤት እንደ ወንድሞቻቸው አባይ ፀሐዬ፣እንደ ፀጋዬ በረሄ፣እንደ አርካቤ ዕቁባይ ፣የኢትዮጵያን ህዝብ “የአስተዳደር፣ደህንነት ኢኮኖሚያዊ ራዕይ ” አሁንም ልወስኑለት አሰፍስፈዋል። የህወሃት ትግራይ የበላይነት የለም” የሚለውን፣ ከአያ ጅቦ ለይቶ በትክክል ጅብ ስለመሆኑ ህዝቡ ከተረዳ ሁለት አስርተ አመታት አለፉ።እኛ የምንለው ደግሞ “የህወሃት ዲሞክራሲ ከላይ ዝረፍ ፣ከታች “ግደፍ”ሆኖ ስለመቆየቱ ለጌታቸው እየገለጽን፣የአሁኑ የፓርቲ ሹመት ወደ በለጠ ውድመት የሚያመራ መሆኑን በማስገንዘብ ጭምር ነው።ይህንን ህዝብ የለመዱት ለትንሽ ጊዜ ሊዘርፉት የችሉ ይሆናል።

እየሰደቡት ግን አብረዉት አይቆዩም።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s