Gumaa Saqeta: “ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት ድርጅት”

እኔ በበኩሌ ሰቀጠጠኝ፡፡ ለእነሱ እኔ አፈርኩ፡፡ ስለ እውነት ማሰቢያ ያላቹህ የህወሀት ተከታዮች ይሄን ጉድ ብቻ ሳይሆን የጉድ ጉድ ከተመለከታቹ ቦሀላ ልታፍሩ፣ልትሸማቀቁ አዎ አንገት ልትደፉ ይገባል፡፡ ይህን እዉነተኛ ታሪክ ያያቹ ለሌሎችም እንድታካፍሉ እጠይቃቹሀለው፡፡

Gumaa Saqeta

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ 

ዛሬ ምሽት ላይ OBN በመሀል ከተማ አዳማ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የኢጣሊያ ማፍያዎች ተግባር ለ12 አመት እንደማያውቅ ነው እያወጋን ያለው፡፡ጎበዝ ይህ ያማልና በደንብ አስቡበት(ከዚህ በታች በጽሁፍ የማቀርብላቹ የሆነውን እውነታ ነው)

.

  -ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ደቨሎፕመንት ድርጅት የተመሰረተው ትግራይ ላይ 1981 ሲሆን አመሰራረቱም በጦርነት የተጎዱ ሰዎችን እና  ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናትን ለመርዳት የተቋቋመ ነው፡፡ ከጦርነቱም ቦሀላ በልመና የሚተዳደሩትን እና መንገድ ላይ ጎዳና የወጡ ለመርዳት ፍቃድ ያገኘ ሲሆን በህገወጥ መንገድ የተያዙ ኮንትሮባንድ ንብረቶችን በነጻ እየወሰደ ከታች በፎቶው ላይ በምናያቸው አዳማ ውስጥ በሚገኙ ሁለት በጣም ትላልቅ መጋዘኖች ውስጥ እቃዎች አጭቆ በየ ቀኑም ከዚህ መጋዘን በተጎታች መኪና ወዳልታወቀ ቦታ ማጋዝ ከጀመረ ሰባት አመት አስቆጥሯል የአዳማ ከተማ አስተዳደር በነዚህ መጋዘኖች ውስጥ ምን እንዳለ እና ይህ ድርጅትም ከተማቸው ዉስጥ መኖሩን እንኳን አያውቁም፣እነዚህ እቃዎችም ወዴት እየተጫኑ እንዳለ እና ህጋዊነታቸውንም ለማረጋገጥ በማለት መጋዘኖቹ እንዲታሸጉ ከተደረገ ቦሀላ አጣሪ ኮሚቴ በማቋቋም ቡድኑ ወደ ትግበራ ሲሰማራ የጉምሩክ ሰራተኞችንም አዋቅረው የታሸገው በር ተከፈተ፡፡በቅድሚያ ብዛት ያላቸው መድሀኒቶች፡፡እነዚህ መድሀኒቶች እንዴት እንደገቡ፣ለምን እዚህ ቦታ ሊገኙ እንደቻሉ፣በየትኛው ፍቃድ ገቡ? ከማን ተገዙ????

…መጋዘኖቹ በሚገራርሙ ውድ እቃዎች የታጨቀ ሲሆን የOBN ጋዜጠኛ እንደ አልባሌ ጣል የተደረገ አንድ የኢንግላንድ ምርት የሆነና ደረጃውን የጠበቀ በሚንስትር ደረጃ የሚለበስ ሱፍ ከፍ አድርጎ በማንሳት የኤሌሻዳይ ድርጅት ተወካይ የሆነችው ንጋትን ጠየቃት፡-

ጋዜጠኛ “ይህን ምንድነው ምታደርጉት…..”በማለት ይጠይቃታል

መልስ፡- “እነዚህ የምታያቸውን…” አለች በየ ቦታው ተዘርግተው የሚታዩትን ሱፍ ልብሶች፣ቶርሽን ጫማዎች፣በእኛ ደረጃ ለመግዛት የማይሞከሩና የማይታሰቡ ጭምር የሆኑትን የፈረንሳይ ሽቶዎች

“የምንሰጠው በልመና ላይ ለተሰማሩ፣ጎዳና ላይ ለወጡ ነው የምንሰጠው” በማለት ምላሽዋን ሰጠች፡፡በመቀጠልም

“…ይህን ስራ የምንሰራው በዋናነት ከፌደራል መንግስት ጋር ነው ለ12አመት ያህል በልመና የተሰማሩትን እና ጎዳና ላይ የወጡትን እየረዳን ሲሆን ቅርንጫፍ ከፍተን የምንረዳውም ትግራይ፣አማራ፣ደቡብ እና አፋር ላይ ነው፡፡ ድርጅታችን ከፌደራል መንግስት ጋር ነው የሚሰራው ኦሮሚያ ላይ ፕሮጀክት የለንም ለመክፈት ግን እየጠየቅን እንገኛለን”በማለት ቁስላችን ላይ ሚጥሚጣ ነስነስ አድርጋ አረፈችው፡፡

.

-ድርጅቱ አዳማ ላይ ማሰባሰብ እንጂ ከመጋዘኑ ፊት ለፊት የሚመገቡትን አጥተው ሌት በብርድ የሚጠበሱትን ወላጅ እና ቤት አልባ ህፃናትን ለመርዳት ለምን ራሮት(መራራትን)አጣ?

.

የኦሮሚያ ክልል ያዋቀራቸው አጣሪ ኮሚቴዎች ግን በድርጅቱ ዙሪያ አለ ምንም ጥርጥር በእርዳታ ድርጅት ስም ከፍተኛ የሆነ የኮንትሮባንድ ሰንሰለት(ፌደራሉን ጨምሮ) እየተካሄደ እንደሆነ በግልፅ አቋማቸውን ገልጸዋል፡፡

.

የቡድኑ መሪም እንዲህ ይላል “..የዚህ ድርጅት መነሻው ችግረኞችን አስታኮ ሲሆን ተግባሩ እና እየሰራ ያለው ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ለሰባት አመት ነው ይህኅ ጉዳይ ሲፈጽሙ የኖሩት፡፡እረዳታን የሚረዳ ድርጅት ከሆነ ምነው እኛ በብዙ ሺህ ችግረኞችን እዚሁ ከተማ ውስጥ አፍስሰን በየቤቱ እየዞርን እርዳታ ስንጠይቅ እንዴት ዝም አሉን?”

.

ሌላው የቁጥጥር አባል ደግሞ እንዲህ ይላል

“….በቀን እስከ ስምንት ተሳቢ መኪና ከዚህ ጭነው ይወጣሉ፡፡ምን እንደጫኑ ወዴት አየጫኑም እንደሆነ ምናውቀው ነገር የለም የሚቆጣጠራቸውም ሰው የለም ”

..

.ከመነሻውስ ይህን በቢሊየን የሚቆጠር ንብረት ለአንድ ድርጅት መስጠት ህጋዊ ነው????

.

እግዚኦ አልኩኝ ለነዚህ እኩያን፡፡እሺ ምን ቀራቸው???ሌላው ይቅር ኮንትሮባንድ የሚያዘውን በጀርባ መውሰድ ምን የሚሉት ግፍ ይሆን፡፡

.

እኔ አበቃሁ፡፡እነሱ ግን እንቅልፍ የላቸውም የጉድ ዘመን፡፡
.

.ለኦሮሚያ ክልል መንግስት ግን ማመስገኛው አቅም የለኝም፡፡

አስታውሱ ከዚህ ሁሉ ተግባር ጀርባ ስንት ሚሊየነር ጀነራል እንዳለ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s