የኦሮሞ ነጋዴዎች ጉዳይ መርዶ ነጋሪም፣  ቀባሪም ያጣ ጉዳይ መሆኑ ማብቃት አለበት።

የኦሮሞ ነጋዴዎች ጉዳይ መርዶ ነጋሪም፣  ቀባሪም ያጣ ጉዳይ መሆኑ ማብቃት አለበት።

Dr Birhanemeskel Abebe Segni

*****************************************

 ትናንት በአንድ የኦሮሞ ንግድ ድርጅት መመረቂያ ስነ ሥረዓት ላይ ክቡር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከፕረዝደንት ለማ መገርሳና ከአፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ጋር መገኘታቸው ብዙዎችን አስደስቷል። አነጋግሯልም።
ሁኔታው ባለፉት 26 ዓመታት ወስጥ መርዶ ነጋሪ እንኳን አጥተው ህወሃት/ኢህዲግ ያጠፋቸውን ሰፈር ቁጥር ያሌላቸው የኦሮሞ ነገዴዎችን ጉደይ እንደስብ አስገደደኝ።
 ካለፉት አስር፣ አስራ አምስት ዓመታት ወዲህ አገራዊ ግንዛቤ ላዳበሩትና ምንም አይነት የኦሮሞ ነጋዴዎችን ላላዩት የኦሮሞ ወጣቶች ኦሮሞ ዱሮም አርሶ አደርና አርብቶ አደር ገጠሬ ብቻና በንግዱ ዓለም ምንም ተሳትፎ እንዳልነበረው ተደርጎ ሲነገር ያስደነግጣል።
 አንዳንድ የህወሃት/ኢህደግ ካዲሬዎችማ አንድ ወይ ሁለት የኦሮሞ ነጋዴዎችን ስም ይጠሩና ህወሃት/ኢህዲግ ያበለፀገው ኦሮሞን ብቻ ነው ብለው ይሳለቃሉ።  ህወሃት/ኢህደግ ስልጣን ከያዘ በኋላ “ፕረዝደንቱ ሁሉ ኦሮሞ ነው። ስልጣን መቼ ነው ለእኛ የሚደርሰው?” እንዳለው የህወሃት ካድሬ አይነት መሆኑ ነው። 
እውነታው ግን በጃኖህም ጊዜ ሆነ በመንግስቱ ኃይለማሪያም አስተዳደር ዘመን አሁን ከለው ቁጥር የተሻለ እኔ ነኝ ያሉ እጅግ የከበሩና የተወደዱ ስመ ጥሩ የኦሮሞ ነጋዴዎች ነበሩ።
 በ1991 ህወሃት/ኢህዲግ አዲስ አበባ ሲገባ ከ230 በላይ የኦሮሞ አስመጭና ለኪ የንግድ ድርጅቶች ነበሩ። አሁን ያ ሁሉ ጠፈቶ አንድ የኦሮሞ ንግድ ተቋም ተከፈተ ሲባል እንደሰታለን። የኦሮሞ ባለሥልጣናትም ተሽቀዳድመው ይገኛሉ። 
ላለፉት 26 ዓመታት ህወሃት/ኢህዲግ የኦሮሞ የፓላቲካ መሪዎችን፣ ሙሁራንን፣ዘፋኞችን፣ተማሪዎችን እና ገበሬዎችን እየገደለ፣ እያሰረና ከአገር እያባረረ መኖሩን ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቃል። 
ነገር ግን የህወሃት/ኢህዲግ መንግስት በኦሮሞ ነጋዴዎች ላይ የፈፀመው መጠነ ሰፊ ጥቃት በኦሮሞ ህዝብም ሆነ በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ተገቢውንና የሚገባውን ትኩረት አላገኘም። የኦሮሞ ነጋዴዎች ያለ መርዶ ነጋሪም፣ ያለ ቀባሪም ነው የቀሩት።
በ26 አመታት ጊዜ ውስጥ ህወሃት/ኢህደግ ሁሉንም ታዋቂ የኦሮሞ ነጋዴዎችን አንድ በአንድ ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ለይቶ አጥፍቷቸዋል። 
 ብዙዎችን አስሮ ወይም ከአገር አባሮ ንብረታቸውንና ንግዳቸውን ወስዳል። ሌሎቹን የግብርና የሙስና ህጎችን እንደመጨቆኛና መዝረፊያ መሳሪያ ተጠቅሞ ከገበያ ውጭ አድርጓቸዋል። 
ኢህዲግ የሙስናና የግብር ህጎቹን ልክ እንደፀረ ሽብር ህጉ ኦሮሞዎችን ብቻ ለይቶ ለማጥፈትና ለማጥቃት ያወጣ ይመስላል። 
ለምሳሌ ህወሃት/ኢህዲግ አዲስ አበባ ሲገባ በኢትዮጵያ በሙሉ ማዳበርያ የሚያከፋፍሉት አንድ የተከበሩ የኦሮሞ ነጋዴ ነበሩ። ህወሃት/ኢህዲግ እሳቸውን አጥፍቶ ንብረታቸውንና ንግዳቸውን ሞዴሉን እንኳን ሳይቀይር ለመውሰድ ቀናት አልወሰደበትም። 
ዛሬ በህገወጥ መንገድና በማን አለብኝነት የተወሰደው የእኝህ የተከበሩ ኦሮሞ ነጋዴ የመደበሪያ ንግድ ሙሉ በሙሉ በህወሃት ድርጅቶች እጅ ነው። 
የኦሮሞ ገበሬ ማዳበሪያ የሚገዛው ከነዚህ የህወሃት ድርጅቶች ነው። አሻሻጮቹና የግዥውን ዋጋ የኦሮሞ ገበሬዎችን አፍንጫቸውን ይዘው የሚቀበሉት ደግሞ የልማት ሰራተኞች ተብለው በመንግስት ደሞዝ እየተከፈላቸው ለማዳበርያ ሻጩ ድርጅት እንዲሰሩ የተቀጠሩ የኦህዲድ ካድሬዎች ናቸው። ድርጅቶቹ ያለ ወጭ ትርፍ መቁጠር ብቻ ነው። 
በተመሣሣይ ሁኔታ ህወሃት/ኢህዲግ አዲስ አበባ ሲገባ የቡና ንግድ ሙሉ በሙሉ በኦሮሞ ነጋዴዎች እጅ ነበር። ዛሬ ህወሃት/ኢህዲግ የቡና ገበያውን ሙሉ በሙሉ ከኦሮሞ ነጋዴዎች እጅ ወስዶ ጨርሶ የቡና እርሻውን ከኦሮሞ ገበሬ እጅ ወደ መቀማት ተሸጋግራል። 
የጫት፣ የቀንድ ከብት፣ የቆዳና ሌጦ፣ የእህል እና ሌሎችም ንግዶች እንደዚሁ በጉልበት በህወሃት/ኢህዲግ ሰዎች ተወስደዋል። የተረፋቸውን የሱማሌ ጃንጃዊድ ሚሊሻ አደራጅተው ህዝባችንን እያስቀሙት ነው። 
በቅርቡ የአወዳይ የጫት ንግድ የገበያ ቦታውን እንቀይራለን ብለው መዳፈራቸው የኦሮሞ ህዝብ ወይ በአገር አለ ወይስ አገር የለውም የሚያስብል ሆኗል። 
የኦሮሞ ነጋዴዎች በኦሮሚያ ላሉት የትምህርት ተቋማት የመማርያ ቁሳቁሶች ማቅረብ አይችሉም። ለዚያ የተመደበው ሌላ ነው። ሌላው ቀርቶ በኦሮሚያ ላሉት ዩንቨርሲቲዎች የተማሪዎች ምግብ አቅራቢዎቹ የኦሮሚያ ነጋዴዎች አይደሉም።
 ሮቤ፣ ነቀምት ወይም ጅማ ላለ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ምግብ አቅራቢዎች ጫረታ የሚከፈተው አዲስ አበባ ላይ ነው። የአከባቢው ነጋዴ ነገረ ስራውን እንኳን ሳያውቅ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እዛው አዲስ አበባ እጅ ይለውጣል። 
በጃኖህና በመንግስቱ ጊዜ በብዛት በኦሮሞ ነጋዴዎች ተይዞ የነበረው የፋርማስ ንግድ አሁን ሙሉ በሙሉ ከኦሮሞ እጅ ወጥቷል። ኦሮሞ በንግድ ችሎታ ማነስ ተሸንፎ ሳይሆን በፓለቲካ በተደራጀ ቡድን ተቀምቶ ነው። 
ህወሃት/ኢህዲግ አንዳንድ የኦሮሞ ነጋዴዎችን የቀማበትን መንገድና የተፈፀመባቸውን ወንጀል መስማት የደም እምባ ያስለቅሳል። አንዳንዶቹን ጊዜ እንደፈቀደ የተፈፀመባቸውን የግፍ ታሪክ ለህዝብ ጆሮ ለማቅረብ እንሞክራለን። 
ብዙዎቹ የኦሮሞ ነጋዴዎች በበረሃ ውስጥ ብቻውን እንደቆመ ዛፍ የሚወርድባቸውን የህወሃት/ኢህዲግ የግፍ ሃሩር፣ ንፋስና ሰይፍ ብቻቸውን የሚቋቋሙበት ሃይሉም ሆነ አቅሙ ስላሌላቸው ጠፍተዋል። አብዛኞቹ ብቸኛና ባታሌ ሰራተኞች በመሆናቸው ከኦሮሞ ህዝብም ጋር ምንም ትስስር የላቸውም። አንዳንዶቹ ከባለ ጊዜዎቹ ጋር መስለው ወይም ገብረው ለመኖር ሲጥሩ በዚያው ተበልተው ጠፍተዋል። ጥቂቶች ዛሬም ቢሆን አዙረው የሚያዩበት አእምሮና አንገት የፈጠረባቸው እንኳን  አይመስሉም። 
ጉዳዩ ብሄራዊ የአስተሳሰብ፣ የፓሊሲና የስትራተጂ ለውጥ ማድረግ ይጠይቃል። የኦሮሞ ነጋዴዎች ያለምንም ማወላወል በግልፅ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር በሃብታቸውና በጉልበታቸው መቆም አለባቸው። የኦሮሞ ህዝብም እነዚህን ነጋዴዎችና ንብረታቸውን ከጥቃት የመከላከል ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለበት።በተለይም  የኦሮሞ ፓሊሶችና ወታደሮች በዚህ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። የኦሮሞ ሙሁራን፣ የፓለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞች ለኦሮሞ ነጋዴዎች ደህንነትና በነፃነት መነገድ ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት ህዝቡን ማስተማርና ጠቃሚ ፓሊሲዎችና ህጎች  እንዲወጡ ማድረግ  አለባቸው። 
የኢኮኖሚ አብዮት እያልን ነባር ነጋዴዎችን ከጥቃትና ከቅሚያ መከላከል ከልቻልን ዛሬ የምንፈጥረውንም ነጋዴ የምናደልበው ነገ ለጠላት የፋሲጋ ሰንጋ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ የለውም። የኦሮሞ ህዝብ በየስራ መስኩ ከውስጡ የሚወጡትን መሪዎች(ነጋዴዎችን ጨምሮ) ከጥቃት መከላከል መቻል አለበት። ግዴታውም ነው።የኦሮሞ ነጋዴዎች ያለ መርዶ ነጋሪና ያለ ቀባሪ የሚቀሩበት ዘመን ብቻ ሳይሆን ነጋዴዎቻችን ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ የሚጠቁበት ዘመን አሁን ማብቃት አለበት።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s