ሞቲ ቢያ: ይድረስ ለአምባገነን ነፍስ ገዳዮች!!

ይድረስ ለአምባገነን ነፍስ ገዳዮች!!

.

ሞቲ ቢያ

.

ወገን በመደበኛ ጦር በአደባባይ ይገደላል። ሕዝብ ያላቅሳል። ድንበር ይጣሳል። የሚገድል ድርጅት ይወደሳል።
ቃላት መግለፅ የማይችለው እብሪት ከገደቡ አልፎአል። ግፍ ገደቡን ጥሶአል። ከባዶ እግር ነፃ ባወጣችሁና ባለቢሊዮኔሮች ባደረጋችሁ ሀዝብ ላይ መዝምቱን መረጣችአል።
እንዲህም ሆኖ እባካችሁ አንድን እውነት እወቁ። ከእንግዲህ እንደ ተለመደው እያወናበዱ መቀጠል አይቻልም። የጦር መሣሪያ ብዛት፣ የሠራዊት ጋጋታ ጊዜያዊ መሆኑን ለእናንተ መንገር አያስፈልግም። ጦርነት የጀመራችሁት ከማን ጋር እንደሆነ የተገነዘባችሁ አይመስልም።
የኦሮሚያ ሕዝብ የኢምፓየርቱ ብዙሃን ሕዝብ ነው። የሀገርቱ እምብርት ነው። የኢኮኖሚ ሃይል ነው።  ጀግና ሕዝብ ነው። በተለይ የአሁኑ ጊዜ ጦርነት ከዚህ ቀደም  ከአሸነፋችሁት፣ ከሀገር ካባረራችሁት ወገን ጋር የምታካሄዱ ኣይነት ጦርነት አይዶለም።  ይህ ሌላ፣ ፊፁም የተለየ ትውልድ ነው።
በቴክኖሎጅ የሚታጋዝ፣ ከውግያ በቀር ሌላ አማራጭ የከለከላችሁት የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ትውልድ  ነው። ትውልድን አታሸንፉም። መንገዳችሁ አይሠራም። እንኩዋንስ ወታደራዊ አገዛዝ፣ ሌላም ተዓምር ቢታመጡ የኦሮሞን ሕዝብ አሸንፋችሁ፣ ሰላምን  ማስፈን አትችሉም። የኢኮኖሚ ብልፅግና አታመጡም።ሕይወታችሁንም አታድኑም።
ስለዚህ ከሕዝብ በስተጀርባ የሚታካሄዱትን ሴራና  ያወጃችሁን ጦርነት አቁሙ። በጀብደኝነት መንገዳችሁ  ከቀጠላችሁ ሥልጣናችሁ በሚያስገርም ፍጥነትና  ባልጠበቃችሁት ሁኔታ ይደመደማል !! የመጭው ጊዜ ዕጣ ፋንታችሁ ፊፃሜ የማይገኝለት ልቅሶ ይሆናል!!
በሌላ በኩል ደግሞ በጀብደኞና ስግብግብ ፖለቲካኞች የተሳሳተ  ፖሊሲ ምክንያት በክልሉ ላይ አደገኛ የእርስ በርስ ጦርነት እያንዣበበ ነው። በምሥራቅ አፍሪካ ሰላም ልኖር የምችለው በሁለቱ ታላላቅ ብሄራት መካከል ዘለቄታዊ ህብረትና ትብብር ሲኖር ብቻ ነው። ሁለቱም ታሪካዊ ቁርኝት ያላቸው የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች ናቸው። በዚህ አጋጣሚ፣ የኦሮሞ ምሁራን የታገሉት የአማራ ገዢ መደቦችን ጭቆና፣ የበላይነትና ትምክህተኝነት እንጂ የአማራን ሕዝብ  አይዶለም። ይህ በሁሉም ዘንድ በቂ ግንዛቤ ሊገኝ ይገባል።  እውነቱ ከተፈለግ፣ ኦሮሞና አማራ በደም የተሳሳሩ ምንም ዓይነት  የፖለቲካ ሴራ የማይለያያቸው ሕዝቦች ናቸው።
ትክክል ያልሆነውን ያአንድ ዘመን የፖለቲካ አካሄድን ማውገዝ ማለት ሁለቱ  ሕዝቦች ጠላት ሆኑ ማለት አይዶለም።   በተላይ ዛሬ ሁለቱን ሕዝቦች ለማቃቃር የሆነ ያሆልነውን ተንኮል የሚሸሩቡ ሁሉ የሁለቱም ሕዝቦች እኩል ጠላቶች  መሆናቸው በውል መታወቅ አለበት።ተፈለገም ተጠላ፣ በአከባቢው  ሰላም ላይ መወሰን የምችሉት ሁለቱ ሕዝቦች ናቸው።አንድነታቸው ተፈልጊ ብቻ ሳሆን ወሳኝም  ነው።
ክቡራን የወያኔ መሪዎችና ጀኔራሎች! በግልፅ እንደሚታውቁት የፖለቲካ አማራጭ አላጣችሁም ወይም አልተከለከላችሁም።ተመካከሩ። በመካከልችሁ የሚያስቸግሩ አክራሪዎች ካሉ አስወግዱ። እነርሱ ጅብደኞች፣ ጥቅም አስዳጆችና ለእውነት ደንታ ቢሶች ናቸው። ከእነርሱ ጋር መቀጠሉን ከመረጣችሁ የእናንተው መጪ ትውልድ በሰራችሁት ግፍ፣ ባፈሰሳችሁት ደም፣ በክልሉ ላይ በፈጠራችሁት ሁከት ምክንያት በእናንተ መጠራትን ይፀየፋል። የምሥራቅ አፍሪካን ለግል ጥቅሙ ሲል እሳት የጫረበት  ክፉ ትውልድ ተብላችሁ ትጠራላችሁ። ዕድሜም፣ ሥልጣንም፣ የፖለቲካና የወታደራዊ የበላይነትም ጊዜያዊ ናቸው።
ትውልድና ታሪክ ግን ይቀጥላሉ። ስለዚህ የሰላም መንገድ ይታያችሁ። ሕዝብ የሀገር ባለቤትነቱንና መብቱን ጠየቀ እንጂ ሙቱ ወይም ከሀገር ውጡ አላላችሁም። ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ፊቱ።  ሽፍጥ ለሌለበት ሰላማዊ የፖለቲካ ድርድር  ራሳችሁን  አቅረቡ። ሁሉም ይተባበራችአል። ተንኮልና ሴራን ተው። ለትንሽ ለትልቁ ሠራዊት ማንቀሳቀሱን አቁሙ። ልካችሁ ያልሆነውን ሱሪ ካልለብስን አትበሉ። በአቅማችሁ ኑሩ። ካልሆነ ከአቅማችሁ በላይ የተሰቀላችሁበት የውሸት ፈዴራሊዝም በቅርቡ ይወድቃል።አሁንም ቢሆን   ወደ ፊፃሜው እየመጣ ነው።
ባጭሩ የኦሮሞን ሕዝብና የታሪክን እውነት አታሸንፉም። ሰላም የሚታገኙት የሰላምና የእውነት መንገድ ሲትከተሉ ብቻ ነው!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s