Leaked TPLF Document: “የፍቅር ቀን”, “የአረጋዊያን ቀን”, “የአንድነት ቀን”, “የመከባበር ቀን”, “የሃገር ፍቅር” …

Leaked TPLF Document: “የፍቅር ቀን”, “የአረጋዊያን ቀን”, “የአንድነት ቀን”, “የመከባበር ቀን”, “የሃገር ፍቅር” …

https://i1.wp.com/www.tigraionline.com/tasset/images/tplf-12th-congress.jpg

 

ተ.ቁ የዝግጅት ዓይነት ዝርዝር ተግባር የተግባር ቀንና ሰዓት ቦታ አስፈፃሚ ፈፃሚ የቀኑ መሪ ቃል

1. ጋዜጣዊ መግለጫ የሃገር ውስጥ እና የውጭ የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ ስለ በዓሉ እና አከባባር ሁኔታው ለጋዜጠኞች መግለጫ ይሰጣሉ፡፡ ነሃሴ 24/2009 ዓ.ም

ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ በኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ክፍታ ነው

1. 2. የበዓሉ መክፈቻ ስነ-ስርዓት የኢ.ፌ.ደ.ሪ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሸመ፣የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ጥሪ የሚደረግላቸው  አዋቂና ታዋቂ ሰዎች እንዲሁም የኪነ-ጥበብና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በተገኙበት

 የዝግጅቱ ጠቅላላ አላማ ይፋ ይደረጋል፡፡

 የአስሩ ቀናት ዝርዝር ተግባር ይፋ ይሆናል፡፡

 ለአስሩ ቀናት ኩነቶች ተጠሪ የሆኑ አካላት ይፋ የሚደረጉ ሲሆን መላ የሃገራችን ህዝብ ተሳታፊ የሚሆንበት መንገድ እና ከህዝቡ የሚጠበቀው የተሳፎ ሁኔታ በዝርዝር ይገለፃል፡፡

ነሃሴ25/2009ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓትበአዲስ አበባ ሸራተን አዲስየኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትየኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ ሸዋፈራው መልቲሚዲያ እና ሠራዊት መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን

አ/አዲስ አበባ መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ክፍታ ነው

ተ.ቁ የዝግጅት ዐይነት ዝርዝር ተግባር የተግባር ቀንና ሰዓት ቦታ አስፈፃሚ ፈፃሚ የቀኑ መሪ ቃል 

2. 3.
የፍቅር ቀን 

ለዚሁ ዓላማ በክልልና በፌደራል ሰንደቅ ዓላማዎች ባሸበረቁ ሁለት መኪናዎች፣ታዋቂ ሞዴሎች በተለያዩ ዲዛይን በተሰሩ ሃገራዊ የባህል አልባሳት ተውበው በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየዞሩ የአበባ ስጦታ ለሁሉም ሰው ያበረክታሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከንቲባ ፊርማ ያረፈበት ቀኑን በሚገልጽ መልኩ የሚዘጋጅ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መግለጫ ፖስት ካርድ ለክቡር ፕሬዝዳንቱ፣ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስተሩ፣ ለፌደራል ምክርቤት አፈጉባኤዎችና ለሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሚኒስትሮች በየጽ/ቤታቸው በሞዴሎቹ አማካኝነት ይደርሳል፡፡

ለሃይማኖት አባቶች በየእምነት ተቋማቸው፣ በየሆስፒታሉ ለሚገኙ ህሙማን፣ ለህግ ታራሚዎች፤ለሕፃናት፣ለእናቶችና አዛውንቶች ክብካቤ መስጫ ተቋማት መልካም ምኞት መግለጫ የፍቅር ስጦታ ፖስት ካርድና አበባ ይበረከታል፡፡

ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ መንግስታዊ ያለሆኑ ድርጅቶች፣የግል መስሪያ ቤቶች እና ሌሎች እዚህ ያልተገለጹ ድርጅቶች በሙሉ በሃላፊዎቻቸው አማካኝነት ለሁሉም ሰራተኞቻቸው የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ ፊርማቸው ያረፈበት ፖስት ካርድና የአበባ በስጦታ ያበረክታሉ፡፡ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተዘጋጁ መድረኮች በዲጄ አማካኝነት የተለያዩ ቀኑን የሚገልፁ ሀገራዊ ሙዚቃዎች ይሰማሉ፡፡ በመድረክ መሪዎች አማካኝነት ስለ ቀኑ በተደጋጋሚ መግለጫ ይሰጣል፡፡ የተመረጡ የውዝዋዜ ቡድኖች በቦታዉ ለሚኖሩ ታዳሚዎች የውዝዋዜ ትርኢት ያቀርባሉ፡፡ የአበባ ስጦታው በዚህ ቦታም ቀጣይነት ኖሮት ይውላል፡፡

የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ማርሽ ባንዶች በከተማዋ ዋና ዋና አደባዮች ትርዒት ያቀርባሉ፡፡

የኢ.ፌ.ደ.ሪ አየር ሃይል ልዩ ልዩ ቀኑን የሚገልፁ መልዕክችን በሄሊኮፍተር ይበትናል፡፡ ነሃሴ26/2009ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉቀን በመላ ሃገሪቱ በተመረጡ እና በሚዘጋጁ አደባባዮችና መድረኮች የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፤ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር በፍቅር የተሳሰር ህዝብ እናት ኢትዮጲያ

ተ.ቁ የዝግጅት ዐይነት ዝርዝር ተግባር የተግባር ቀንና ሰዓት ቦታ አስፈፃሚ ፈፃሚ የቀኑ መሪ ቃል 

3. 4. የእናቶች እና ህፃናት ቀን

የኢ.ፌ.ደ.ሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና የኢ.ፌ.ደ.ሪ የሴቶችና ሕፃናት ሚኒስቴር ኃላፊዎች የእናቶችና የሕፃናት መርጃ ተቋማትን ይጎበኛሉ፡፡ በተለያዩ የብዙሃን መገናኛ ተቋማት መልዕክት በማስተላለፍ በእናቶች እና ሕፃናት ጤና ላይ የግንዛቤ መስጫ መድረክ ይፈጥራሉ፡፡

የብዙሃን መገናኛዎች በርዕሰ ጉዳዩ ላይ እንግዳ በመጋበዝ በማህረሰቡ ላይ የግንዛቤ መስጫ ዘመቻ ይፈጥራሉ፡፡

በሁሉም ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት በእለቱ የሚወልዱ እናቶችና የተወለዱ ሕፃናትን በልዩ እንክብካቤ በማስተናገድ ስማቸውን በልዩ መዝገብ ላይ ያሰፍራል፡፡ እነዚህ እናቶችና ሕፃናት የኢ.ፌ.ደ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ፊርማቸውን ያኖሩበት የመልካም ምኞት መግለጫና ለሕፃናቱ ታሪካዊና እድለኛ አዲስ ትውልድ መሆናቸውን የሚያበስር ካርድ የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡

በየአደባባዮች ያሉት መድረኮች ቀኑን በሚገልጹ ዜማዎች ይደምቃሉ፡፡ በፕሮግራም መሪዎችና መድረኩን በሚከፍቱ እንግዶች መልዕክት ይተላለፋል፡፡ የተዘጋጁት የውዝዋዜ ቡድኖቹ ትርዒታቸውን ሲያቀርቡ ይውላሉ፡፡ ነሃሴ 27/2009 ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉቀን በመላ ሃገሪቱ በተመረጡ እና በሚዘጋጁ አደባባዮች፤ መድረኮችና  በሁሉም የጤና ተቋማት የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣   የሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ክብር ለእናቶች ፍቅር ለህፃናት

ተ.ቁ የዝግጅት ዐይነት ዝርዝር ተግባር የተግባር ቀንና ሰዓት ቦታ አስፈፃሚ ፈፃሚ የቀኑ መሪ ቃል 

4. 5 የአረጋዊያን ቀን

በእለቱ ለአረጋዊያን ልዩ ክብር እና እንክብካቤ እንዲሁም የተለየ ፍቅር ይሰጣቸዋል፡፡

የኢ.ፌ.ደ.ሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመሆን የመቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን ማገገሚያ ማእከልን ይጎበኛሉ፡፡ ማዕከሉ እያስገነባ ያለውን ሁለገብ የአረጋዊያን ማዕከል ያለበትን ደረጃ ያያሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከተለያዩ የስራ ኃላፊዎች እና ከየክፍለ ከተማው የበላይ ኃላፊዎች ጋር በከተማቸው የሚገኙ የአረጋዊያን መንከባከቢያ ተቋማትን ይጎበኛሉ፡፡

የብዙሃን መገናኛዎች በርዕሰ ጉዳዩ ላይ እንግዳ በመጋበዝ በማህረሰቡ ላይ የግንዛቤ መስጫ ዘመቻ ይፈጥራሉ፡፡

በየአደባባዮች ያሉት መድረኮች ቀኑን በሚገልጹ ዜማዎች ይደምቃሉ፡፡ በፕሮግራም መሪዎችና መድረኩን በሚከፍቱ እንደግዶች መልዕክት ይተላለፋል፡፡ የተዘጋጁት የውዝዋዜ ቡድኖቹ ትርዒታቸውን ሲያቀርቡ ይውላሉ፡፡ ከሁሉ በላይ በላይ በመላው ኢትዮጵያ በየአካባቢው አረጋውያንን የመንከባከብ፣ ቤታቸውን የማደስ ፣የመጎብኘትና ፍቅር የመስጠጥ ስራዎች በህብረተሰቡ ይከናወናሉ፡፡

ነሃሴ28/2009 ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ ቀንበመላ ሃገሪቱ በተመረጡ እና በሚዘጋጁ አደባባዮች፤ መድረኮችና  በሁሉም በከተማዋ ባሉ የበጎ አድራጎትና የአረጋዊያን መገኛ ተቋማትየኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትየኢ.ፌ.ደ.ሪ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን የዛሬዋን ኢትዮጵያን ለሰሩልን አረጋዊያን ክብር እንሰጣለን
ተ.ቁ የዝግጅት ዐይነት ዝርዝር ተግባር የተግባር ቀንና ሰዓት ቦታ አስፈፃሚ ፈፃሚ የቀኑ መሪ ቃል 

5. 6 የአንድነት ቀን

በእለቱ ሁሉም በስልጣን ፣በትምህርት ደራጃ፣ በሃይማኖት፣በጾታ፣በእድሜ ሳይለያይ ሁሉም በየአካባቢው ተማሪዎች ትምህርት ቤታቸውን ማጽዳት፣ ሰራተኞች የስራ ቦታቸውን ማፅዳትና የማደራጀት ስራ ይሰራል፡፡ የአቅመ ደካሞችን ቤት የመጎብኘትና የመጠገን በአጠቃላይ የበጎ ፍቃድ ስራ በአብሮነት ስሜት በጋር የሚከወን ይሆናል፡፡

የሁሉም የእምነት ተቋማት መሪዎች እና የተመረጡ አዋቂ ሰዎች በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር የሚተዳደሩ እና በመዲናዋ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች በመሄድ ታራሚዎችን ይጎበኛሉ፡፡ ጉብኝታቸው ሙሉ የሚዲያ ሽፋን የሚሰጠው ይሆናል፡፡

በመዲናዋ የሚገኙ የብዙሃን መገናኛዎች በርዕሰ ጉዳዩ ላይ እንግዳ በመጋበዝ በማህረሰቡ ላይ የግንዛቤ መስጫ ዘመቻ ይፈጥራሉ፡፡

በየአደባባዮች ያሉት መድረኮች ቀኑን በሚገልጹ ዜማዎች ይደምቃሉ፡፡ በፕሮግራም መሪዎችና መድረኩን በሚከፍቱ እንደግዶች መልዕክት ይተላለፋል፡፡ የተዘጋጁት የውዝዋዜ ቡድኖቹ ትርዒታቸውን ሲያቀርቡ ይውላሉ፡፡ ነሃሴ 29/2009ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ ቀን በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ ቋሚ መድረኮች እና በፌደራል መንግስቱ በሚተዳደሩ ማረሚያ ቤቶች የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባዔ እና የፌደሬሽን ምክርቤት አፈጉባዔ ጽ/ቤቶች

አዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ኢትዮጵያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሄራዊነቱ

ተቁ የዝግጅት ዐይነት ዝርዝር ተግባር የተግባር ቀንና ሰዓት ቦታ አስፈፃሚ ፈፃሚ የቀኑ መሪ ቃል 

6. 7 የንባብ ቀን

በእለቱ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር አቅራቢነት ቁጥራቸው አንድ መቶ የሆኑ ህፃናት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር የፎቶ መነሳት ስነ-ስርዓት የሚከናውኑ ሲሆን በዋናነት ክቡር ጠ/ሚኒስትሩ ለመላው የኢትዮጵያ ታዳጊ ህፃናት አንድ አንቀፅ ከተመረጠ መፅሃፍ ላይ በማንበብ ስለ ንባብ ጥቅም መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡

በየአደባባዮቹ የተዘጋጁት መድረኮች ከጠዋት የፕሮግራሙ መክፈቻ ጀምሮ በየቢሮው ኃላፊዎች መልዕት የሚተላለፍበትና ከመረጧቸው መፅሃፎች ላይ ለታዳሚው የሚያነቡበት ስነ-ስርዓት ይኖራል፡፡ በመድረክ መሪዎች የተለያዩ መልዕክቶች ይተላፋሉ፡፡ በወጣቶች የሚዘጋጁ ልዩ ልዩ ክውን ጥበቦች ለህዝብ ለእይታ ይቀርባሉ፡፡ በዲጄ ሙዚቃና በተወዛዋዦች ቀኑ ደምቆ የሚውል ይሆናል፡፡ በላይብረሪዎች፣ በመጽሐፍት ቤቶች፣ እንዲሁም በወጣቶች ማዕከላት ንባብ ይካሄዳል፤

በመላው ኢትዮጵያ ከፌደራል እስከ ወረዳ ንባብ እና የማንበብ ባህልን ስለማዳበር ይነገራል፡፡ ታዋቂ ደራሲያንና  ምሁራን በየአካባቢያቸው የጉዳዩ ባለቤት በመሆን ሃላፊነታቸው ይወጠሉ፡፡ ነሃሴ30/2009ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉቀን በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ ቋሚ መድረኮች እና በኢ.ፌ.ደ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ንባብን ባህላችን እናደርጋለን

ተቁ የዝግጅት ዐይነት ዝርዝር ተግባር የተግባር ቀንና ሰዓት ቦታ አስፈፃሚ ፈፃሚ የቀኑ መሪ ቃል 

7. 8 የአረንጓዴ ልማት ቀን

በዚህ ቀን በመላ ሀገሪቱ መላው ህዝብ ስለ አረንገጓዴ ልማት ጥቅም በአንፃሩ እና ድርቅ እያስከተለው ያለውን ጉዳት እንዲረዱ የማድረግ ተግባር ይከናወናል፡፡

በሁሉም የብዙሃን መገናኛ ለርዕሰ ጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተሰሩ ለህዝብ እይታ ይቀርባሉ፡፡

የኢ.ፊ.ደ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የኢ.ፌ.ደ.ሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሚኒስትሮች፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከነካቢኔዎቻቸው፣ የሁለቱም የፌደራል ምክር ቤት አባላትና አፈጉባዔዎች፣ ሚኒስትር ድኤታዎች፣ ኮሚሽነሮች፣ አምባሳደሮች፣ ጄነራሎች፣ አዋቂና ታዋቂ ግለሰቦች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ የክልል መስተዳድር ርዕሰ መስተዳሮች፣ የዞንና የወራዳ አስተዳዳሪዎች ለህዝቡ አርዕያ በመሆን በየአቅራቢያቸው  የሚገኙ በክረምቱ የተከናወኑ የችግኝ ተከላ፣ መንከባከብ እና የድርቅ መከላከል ስራዎችን ይጎበኛሉ፡፡

በየአደባባዮች ያሉት መድረኮች ቀኑን በሚገልጹ ዜማዎች ይደምቃሉ፡፡ በፕሮግራም መሪዎችና መድረኩን በሚከፍቱ እንደግዶች መልዕክት ይተላለፋል፡፡ ዿግሜ01/2009ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉቀን በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ ቋሚ መድረኮች እና በሚመረጡ የችግኝ መትከያ ቦታዎች የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር
አ/አበባ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጠበቆች ነን

ተ.ቁ የዝግጅት ዐይነት ዝርዝር ተግባር የተግባር ቀንና ሰዓት ቦታ አስፈፃሚ ፈፃሚ የቀኑ መሪ ቃል 

8. 9 የመከባበር ቀን

በመላው ኢትዮጵያ አረጋውያንን ፣ህፃናትንና አካል ጉዳተኞችን በሁሉም ቦታ ቅድሚያ የመስጠት ፣መንገዶችን የማሻገር፣ ሁለም አሸከርካሪዎች በትግስት ለእግረኞች ቅድሚያ የሚሰጡ ይሆናል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያያን ከወትሮው በተለየ መልኩ በፍቅርና በመከባበር ልባዊ መነሳሳት እርስ በእርስ ያላቸውን አክብሮት የመግለፅ ተግባር ያከናውናሉ፡፡

የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት አካላት እርስ በእርሳቸው ወታደራዊ ሰላምታ ይለዋወጣሉ፡፡

በእለቱ በየአደባባዩ ለዚሁ ስነ-ስርዓት በተዘጋጁት መድረኮች በመታገዝ፣ በመላው የብዙሃን መገናኛ ተቋማት በሚሰጥ መረጃ በመደገፍ ከፌደራል እስከ ወረዳ ባለው አተገባበር የኢትዮጵያ ልጆች በአጠቃላይ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያለንን አክብሮት የምንገልፅበት ስነ-ስርዓት ይከናወናል፡፡

የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ማርሽ ባንዶች በከተማዋ ዋና ዋና አደባዮች ከቀኑ 6፡00-7፡00 ትርዒት ያቀርባሉ፡፡ ዿግሜ 02/2009ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ ቀን በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ ቋሚ መድረኮች ፣በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በኢትዮጵያ በተመዘገቡ መርከቦች፣ በፖሊስና መከላከያ ሰራዊት ካምፖች በየእዙ፣ በሁሉም የመንግሰት እና የግል ተቋማት፣ በመላው አለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንፅላ ጽ/ቤቶች የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በኢ.ፌ.ደ.ሪ የፌደራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር

አ/አበባ ኮሙዩኒኬሽን፣ መከላከያ ሚኒስቴር፣ ውጭጉዳይ ሚኒስቴር፣ ትራንስፖርት ሚ/ር የራሳችን እንዲከበር የሌሎች ማክበር ዘመናዊነት ነው

ተ.ቁ ዝግጅት ዝርዝር ተግባር የተግባር ቀንና ሰዓት ቦታ አስፈፃሚ ፈፃሚ የቀኑ መሪ ቃል 

9. 10 የሃገር ፍቅር

ቀን በመላው ኢትዮጵያ በየትኛው የስራ ቦታ፣ በእያንዳዱ አደባባይ እና መንገድ፣በውጭ ሃገር የኢትዮጵያ አምባሲዎችና ቆንስላ ፅ/ቤቶች ሰንደቅ አላማችን በኩራት ከፍ ብሎ ይውለበለባል፡፡

በእለቱ ልክ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት እስከ 6፡05 በተመሳሳይ ሰዓት ብሄራዊ መዝሙር በሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ይዘመራል፡፡

ይህ ስነ-ስርዓት የንግድ ተቋማት በዲጄዎቻቸው፣ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን፣ በየመንገዱ ያሉ ሶኒክ ስክሪኖች፣ ሁሉም ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች በመኪናዎቻቸው ስፒከሮች፣ የግል አሽከርካዎች፣ የመንግስት እና የግል መስሪያ ቤቶች፣ የመከላከያና ፖሊስ ሰራዊት መስሪያ ቤቶችና ካምፖች የድምፅ ማጉያ ወደ አደባባይ በማውጣት ስነ-ስርዓቱን የሚመሩት ይሆናል፡፡

ስነ -ስርዓቱ በውጭ ሃገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች፣ በበረራ ላይ ያሉ የኢትዮጵያ አየር መንገዶች በዋና ካፕቴኖቻቸው፣ የባህር ትራንስፖርት ሰጭ መርከቦች በዋና ካፕቴኖቻቸው እየተመራ የሚከናወን ይሆናል፡፡

በአዲስ አበባ በፌደራል ፖሊስና የሃገር መከላከያ ማርሽ ባንድ በየክልል ከተሞች የሚገኙ የማርሽ ቡድኖች በዋና አደባባዮች በመውጣት ስነ-ስርዓቱን ይመራሉ፡፡

በእለቱ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ለአምስት ደቂቃ ብቻ በመላው ሃገሪቱ እና ከላይ በተጠቀሱት ሌሎች ቦታዎች ሁሉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ይቆማል፡፡ (የትራንስፖርት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው ይሆናል)፣ በሰዓቱ ለአምስት ደቂቃ በየትኛውም ቦታ የስራ እንቅስቃሴ ይቆማል፣ ከብሄራዊ መዝሙር ውጭ ምንም አይነት ድምፅ አይሰማም፡፡በየአደባባዩ ያሉት መድረኮች ስነ-ስርዓቱን እየመሩ፣ መልዕክት እያስተላለፉ፣ ትርኢት እያቀርቡ የሚውሉ ይሆናል፡፡   ዿግሜ03/2009ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉቀን በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ ቋሚ መድረኮች ፣በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በኢትዮጵያ በተመዘገቡ መርከቦች፣ በፖሊስና መከላከያ ሰራዊት ካምፖች በየእዙ፣ በሁሉም የመንግሰት እና የግል ተቋማት፣ በመላው አለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንፅላ ጽ/ቤቶች የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣  ኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር፣ የ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመገናኛ ና ትራንስፖርት ሚኒስቴር

ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ፣ አ/አበባ ኮሙዩኒኬሽን፣ እጃችን እስኪሻክር እንሰራለን ምክነያቱም ኢትዮጵያን እንወዳታለን

11 የሰላም ቀን

በእለቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አቅሙ በፈቀደው መጠን በስራቦታም ይሁን በመዝናኛ ስፍራ፣ በእምነት ተቋማትም ይሁን በሌላ አካባቢ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን የባህል ልብስ ይለብሳሉ፡፡

ከፌደራል እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ የመንግስም ይሁን የግል መስሪያ ቤት ኃላፊዎች የባህል ልብስ ለብሰው የሰላም ቀዳሚ አርዕያ መሆናቸውን ያሳያሉ፡፡

በሁሉም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚኖሩ ስርጭቶች በተለይ የቀጥታ ስርጭት ፣የዜና እወጃ እና ፕሮግራም አስተላላፊ ጋዜጠኞች ሁሉም ነጭ የባህል ልብስ ይለብሳሉ፡፡

በመላው የኢትዮጵያ አደባባይ እና መንገዶች፣በውጭ ሃገርም በኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ፣በሁሉም የመንግስት እና የግል መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነጭ ባንዲራ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ኣላማ ጎን ይውለበለባል፡፡ በሁሉም የሃገሪቱ ክልል ውስጥ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጁትን ነጫጭ ባንዲራዎች በተሸከርካሪዎቻቸው ላይ በማድረግ ለሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያሉ፡፡

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በክልል ከተሞች በየከተሞቻቸው አደባባይ ላይ ልክ  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ነጫጭ እርግቦች ወደ ኢትዮጵያ ሰማይ ይለቀቃሉ፡፡ በተመሳሳይ ነጫጭ በአየር የተሞሉ በርካታ በራሪ ፊኛዎች በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ይለቀቃሉ፡፡ ዿግሜ04/2009ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉቀን በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ ቋሚ መድረኮች ፣በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በኢትዮጵያ በተመዘገቡ መርከቦች፣ በፖሊስና መከላከያ ሰራዊት ካምፖች በየእዙ፣ በሁሉም የመንግሰት እና የግል ተቋማት፣ በመላው አለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንፅላ ጽ/ቤቶች የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ፣ኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር፣ሸዋፈራው መልቲሚዲያ እና ሠራዊት መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን

አ/አበባ ኮሙዩኒኬሽን፣ የሰላም ዋጋው ውድ ነው

ተቁ የዝግጅት ዐይነት ዝርዝር ተግባር የተግባር ቀንና ሰዓት ቦታ አስፈፃሚ ፈፃሚ የቀኑ መሪ ቃል 

12 የኢትዮጵያን ቀን

ባለፉት አስር ቀናት በየአደባባዩ የተከናወኑ  ተግባራት ተጠናቅረው በተለያዩ ኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች በመድረክ ተከሽነው በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በቻናል አንድ በቀጥታ ስርጭት ለመላው አለም የሚደርስ ይሆናል፡፡

እኩለ ለሊት ላይ ደማቅ ርችት በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ይተኮሳል፡፡ ዿግሜ05/2009ዓ.ም  ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉቀን አዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የኢ.ፌ.ደ.ሪ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ፣ የአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን፣ ሠራዊት መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽንና ሸዋፈራው መልቲ ሚዲያ

እኛ ኢትዮጵያውያን የጥቁር ህዝቦች ተምሳሌት  ነን

https://doc-0c-bc-docs.googleusercontent.com/docs/securesc/ha0ro937gcuc7l7deffksulhg5h7mbp1/jhrofq60jr5viulem0v9ojrttga42f4k/1504015200000/07318319027397249512/*/0BygoyxL0MrF-TW5zVWhJX19SZEU?e=download

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s