​ ኒሞና ቦርቶላ: ግልፀ ደብዳቤ… ለኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ ለኦቦ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ

ግልፀ ደብዳቤ… 

ለኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ 

ለኦቦ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ
ጉዳዪ፣ “ድንገት” ሰለ ተሰራ የእሬቻ እልቂት መተሰቢያ ሀውልትን የሚመለከት ነው።
ክቡር ኦቦ አዲሱ አረጋ?
    በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ በየዓመቱ የሚከበረው የእሬቻ በዓል ተወዳጅ፣ተናፋቂ እና ሚልዪን ኦሮሞዎች በአንድ ጊዜ በአንድ ቦታ በኦሮሚያ እንብረት በሆነችው ቅዱስ ሰፍራ በሆራ አርሰዲ ቡሾፍቱ ከተማ እንደሚከበር ይታወቃል።

   ይህ ክብረ በዓል ወይም ለዋቃ ምሰጋና የማቅረብ ሰነ ሰርዓት ከትውልቀ  ትውልድ እየተላለፈ የመጣ የኦሮሙማ መገለጫ ሲሆን በየዓመቱ የባዓሉ ተሳታፊ ቁጥር እየጨመረ፣ እያደገ እየተመነደገ የመጣ ከመላው ኦሮሚያ አልፎ ለአገራችን ኢትዪጵያ ታላቅ የቱሪሰት መሰህብ እና በዓለም አቀፍ መድረክ እንድትጠራ የሚያደረግ ታላቅ በዓል ነው።

   ይህ ሰላማዊ እና ሀይማኖታዊ በዓል በየዓመቱ የኦሮሞ ህዝብ በዛች ጠባብ ቦታ ፈጣሪውን አመሰግኖ የተራራቀ ተገናኝቶ፣ ፍቅሩን ተለዋውጦ፣ ተድሰቶ ተመራርቆ “የከረሞ ሰው” ይበልን ብሎ ቀጠሮ ተሳጥቶ በምርቃት የሚለያይበት መሆኑ በግልፀ ይታወቃል።እኛም በተደጋጋሚ የበዓሉ ተሰታፊ በመሆናችን የዓይን ምሰክሮች ነን።

   በኦክቶበር ሁለት /ሁለት ሺ አሰራ ስድስት /ግን በገዳ አባቶች የተጀመረው የምርቃት እና የእንኳን አደረሳችሁ ፀሎት፣ ድምዳሜው ሚልዪኖችን ያሸበረ፣በመቶ የሚቆጠሩትን ህይውት የቀጠፈ፣ በኦሮሞ ታሪክ “ጥቁር ቀን” ተብሎ የተመዘገበ፣ አባቶች ጉልበት እና ጭንቅላታቸውን አገናኝተው ያነቡ፣ እናቶች መቀነታቸውን አጥብቀው ድረታቸውን እየደለቁ ለተቀጠፋ ልጆቻቸው ደም እንባ ያለቀሱ፣ ቄሮዎች ለወገኖቻቸው እልቂት የተቃጠሉበት ቀን ሆኖ አልፏል።

   ክቡር አቶ አዲሱ? ይህ ቀን ዋቃ ከሰማይ ቁጣ አምጥቶ ሳይሆን የእርሶ መንግሰትና የፌዴራል መንግሰት በመተባበር፣ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ለማድረግ ታሰቦ ታልሞበት፣ በሰማይ በሂሊኮፐተር በምድር በብረት ላባሽ መኪና ጥይት እና በአነጣጥሮ ተኳሽ ወታዳሮች “በድንገት” ሳይሆን እቅድ ተይዞበት የተፈፀመ እልቂት እንደሆነ የእርሶ ልቦናም፣ መንግሰቶም ሆነ ዋቃ እና ሴይጣን የሚያውቁት ጉዳይ ነው።

      በመሆኑም ይሄ በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ውሰጥ በአሰቃቂነቱ ወደር የማይገኝለትን፣ ያውም መረጃው በዚህ በሃያ አንደኛው ክ/ዘመን በእያንዳንዱ ሰው ኪሰ ውሰጥ በሚገኝ ዶክሜንት እንዴት ህዝቡን በትንቁ ነው ” በድንገት” ለተሰውት ተብሎ የመታሰቢያ ሀውልት ለመሰራት የደፈራችሁት? 

    ይህ የእሬቻ ታሪክ እልቂት የመቶ ዓመት ታሪክ ሳይሆን የአንድ ዓመት የኦሮሞ ህዝብ የቁስል ክሰተት ነው።በምን ሞራል እና እሳቤ ነው የዚህን ታላቅ ህዝብ ቁስል “ድንገት” በመኪና አደጋ ያለቁ አሰመሰሎ ሀውልት ማቆም? የእርሶና የመንግሰቶዎ አቋም ነው ወይስ በትዕዛዝ የተሰራ የፖለቲካ ትርፍ መሰብሰቢያ ድንጋይ ነው?

    እኔ በግሌ እንደ አንድ የኦሮሞ ልጅ ተወላጅ እና በእልቂቱ መቼም የማላገኘውን ውድ ጓደኛዪን አጥቻለው። የእኔ ቢጤ ኦሮሞ ደግሞ በሚልዪን የሚቆጠር ነው። በመሆኑም ከልብ ከአለቀሱ እንባ አይገድም እና ይህ የንቀት ሀውልት ትክክለኛ እልቂቱን የሚገልፀ

የኦሮሞ ህዝብ ዋቃን ለማመሰግን በተሰበሰበበት ቅዱስ ሰፍራ በመንግሰት ታጣቂዎች በሰማይና በምድር በተለቀቀባቸው እሳት ከዚህ ዓለም የተለዪ ሰማዕታት ተብሎ በግልፀ መፃፍ አለበት። ካለሆነ በሚቀጥለው የእሬቻ በዓል ይህ በቀል የሚቀሰቀስ “በድንገት” ያለቁ የሚለው አባባል ህዝቡ ወደ አመድነት እንደሚቀይረው ምንም ዋስትና የላችሁም። የኦሮሞ ህዝብ እና የእርሶ ክልላዊ መንግሰት የሰማይ እና የምድር ያህል እንደ ተራራቃችሁ የተገለፀላችሁ አይመሰለኝም።

   ለማሰታውስ ያህል ፎቶዎቹን አያያዤለው።እባካችሁ ለኦቦ አዲሱ ሼር አድረጉልኝ? Dhiiroo?

ከአሮሞ ሰፋ ጋር!!!
ኒሞና ቦርቶላ
ኦገሰት 27/2017

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s