የሁለት ትውልዶች ወግ! ( ወያኔና ቄሮ )

*******************

By Birhanu Bedane Ayyana

https://www.nazret.com/wp-content/uploads/2016/09/tigray-tplf-40.pngየወያኔ ትውልድ የትግራይ ሕዝብ ብሶት ከ 40 ዓመት በፊት አምጦ የወለደው ቄሮ ነው ። ቄሮ ደግሞ አሁን ላይ የኦሮሞ ህዝብ ብሶት አምጦ የወለደው ወያኔ ነው ። ልዩነታቸው የውልደታቸው ዘመን እንጂ አንድና አንድ ናቸው። ወያኔና ቄሮ ! ልዩነታቸው ወያኔ የትግራይን ህዝብ ብሶት ለማስቀረት የዛሬ 40 ዓመት በረሃ ወርዶ ነፍጥ በማንሳት ፥ እሳት ተሸክሞ እሳት እየተፋ ፥ እየገደለና እየሞተ ፥ ተራሮችን ሳይቀር በባሩድ አረር እያሳረረ አራት ኪሎ መድረሱ ነው ።
አራት ኪሎ ደርሶም እራሱን ” ተራሮችን ያቀጠቀጠ ትውልድ ! ” ብሎ በትዕቢት ጠራ ። መጥራት ብቻ አይደለም ማንም እኔ ባለፍኩበት መንገድ አልፎ ተራሮችን ሊያንቀጠቅጥ አይችልም ብሎ እራሱን አሳመነ ። ስህተቱ እዚህ ላይ ነው !
ለወያኔ ዘመንም ፥ ታሪክ የሚሰራበት መንገድና ታሪክ ሰሪ ትውልድም እሱና እሱ ብቻ ነው ። ግን ይኼ አመንክዮ ዘላለማዊ እውነት ሆኖ ሊሰራ እንደማይችል ፈረንጆቹ “ nothing lasts forever “ እያሉ ይገልጹታል ።
https://i2.wp.com/sunatimes.com/uploads/article/photo/IMG_FC84E3-91C59E-1AADB1-C007C6-E714B9-BE654C.jpgዛሬ ላይ ወያኔ ተወልዶ ከጎለመሰ ከ 40 አመት በኋል የኦሮሞ ህዝብ ብሶት አምጦ የወለደው ቄሮ የተወለደበት ዘመን ከወያኔ ዘመን ትውልድ ጋር የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃል ። ዛሬ ላይ ተራሮችን አይደለም ጎዳናዎችንም ጭምር አንቀጥቅጦ እያሳየን ነው ። ቄሮ ! ይህን ለማድረግ ግን እንደ ወያኔ በረሃ ወርዶ እሳት የሚተፋ ነፍጥ ተሸክሞ መግደልና መሞት አልጠየቀውም ። ምክንያቱም ዘመኑ ነዋ ! ከዘመን ጋር ደግሞ ቢችሉ ኖሮ ሳዳምና ጋዳፊ ነበሩ ትንቅንቅ የሚገጥሙት ። ግን አልቻሉም ! ምክንያቱም ዘመን የራሱን ጀግና የሚፈጥርበት የራሱ መንገድ አለው ።
አሁን ዘመኑ ሌላ ጀግናን ፈጥሯል ። ቄሮን ! የቄሮ ሰላማዊ የትግል መንገድ ስልጣንን ከጥንት ጀምሮ በፍጹም ሰላማዊና የፍቅር መንገድ የሚቀባበልበት የገዳ ስርዓት ትውፊት ባለው የኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ሙሉ ድጋፍ እንደተቸረው እያየን ነው ። እራሳችንን ካላሞኘን በስተቀር ። መቼም መለስ ዜናዊን እንድ መልአክ እንዲታይለት የሚፈልግ ቡድን የኦሮሞ ሕዝብ እነ ዶ/ር መረራና በቀለ ገርባ የመሳሰሉ ልጆቹ እንደ በግ እንዲታዩልት ይፈቅዳል ብሎ ማሰብ ምን የሚሉት ነገር እንደሆነ አይገባኝም ።
ለማንኛውም የኦሮሞ ሕዝብ በልጆቹ በኩል እያነሳቸው ላሉ መሰረታዊና ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎች በንቀት ሳይሆን በአክብሮት ተመልክቶ መልስ መስጠት እንደሚገባ ዛሬም እንደ ዜጋ እመክራለሁ ።

——————//—————–

23 – 08 – 17