Gadaa (Tesfaye) Gebre’ab: ሁለት ቀናት – በOSA ጉባኤ

Monday, July 31, 2017

ሁለት ቀናት – በOSA ጉባኤ

የOSA ኮንፈረንስ ተጠናቀቀ። ጁላይ 29 እና 30 ቅዳሜና እሁድ!! 
ለዘመናት በስም የምናውቃቸው አንጋፋ ሰዎች በተቆነጠረች ሚጢጢ ሰአት ውስጥ እንደምንም አንዳንድ ነጥቦችን ለማንሳት ችለዋል። ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ዋና ተናጋሪ ስለነበሩ ሰፋ ያለ ጊዜ አጊኝተው ነበር።  ስለ ገዳ ስርአት እና የኦሮሞዎችን ጥንታዊ የስነከዋክብት ምርምር አቀረቡልን። ልብ የሚሰቅል ነበር።

በኮንፈረንሱ ላይ ብዙ ሰዎችን አገኘሁ። እነ ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰን፣ አሰፋ ጃለታ፣ ህዝቅኤል ጋቢሳ, አስፋው በየነ፣ ከለንደን ሞሲሳ ራጋሳ፤ ከኖርዌይ አስናቀ ኢርኮ፣ ቦኒ ሆሎኮምብ…ተፈሪ ንጉሴ – ከኖርዊች ዩኒቨርሲቲ፣ ታየ ናዲ፣ ዘልአለም አበራ፣ ሳሙኤል ጋላታ፣ ቶሎሳ ዳቅሲሳ፣ መኩሪያ ቡልቻ፣ አለማየሁ ደበሎ፣ አለማየሁ ኩምሳ፣ ተፈሪ መርጎ – ከዋተርሎ ዩኒቨርሲቲ …ሄኖክ ጋቢሳ፣ ፣ ቤካን ጉልማ፣ ደረጀ ሃዋዝ፣ ገረሱ ቱፋ እዚያው ነበሩ።ሴቶችም ነበሩ። አያንቱ ቲቤሶን አየሁዋት። አማኒ በዳሶ የምትባል ልጅ ከዚህ ቀደም አላውቅም ነበር። ጥሩ ተናጋሪ ነበረች። ስጠይቅ የዶክተር ኑሮ ደደፎ ልጅ መሆኗን ተረዳሁ። አንድ ወጣት ነጭ መጣና በፊንፌኔ አማርኛ አናገረኝ። 
ዶክተር አባድር ኢብራሂም ሲሆን፡ አባቱ ሩስያዊ ነው። በእናቱ አደሬና ሶማሊያ ነው። ስለዚህ ሰው ሰምቼ አላውቅም ነበር። ኢሳት ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ እንደነበር ግን ነገሩኝ።  ያገኘሁዋቸውን ሰዎች ስም ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም። ኦሮሚያ ራሷ እዚያው ነበረች። ጃዋር መሃመድን አላየሁትም።  “ለምን አልመጣም?” ብዬ ስጠይቅ “የOMN አዲስ ቢሮ ለመክፈት ስራ በዝቶበታል” ብለው ነገሩኝ። 

ዶክተር ዲማ ነገዎን አገኘሁት፣

“ኦቦ ዲማ! የቀድሞ አለቃየ!” ብዬ በሞቀ ሁኔታ ጨበጥኩት።

እየሳቀ እንዲህ አለ፣

“አለቃው ማን እንደነበር እንኳ ግልጽ አልነበረም!” 

እውነቱን ነው። ዲማ የማስታወቂያ ሚኒስትር በነበረ ጊዜ አንታዘዘውም ነበር። በጎን የሚያዘን ቴክሱ በረከት ስምኦን ነበር። እና ታዲያ ዲማ እንደ ጉቤሳ ዳቦ ሆኖ ነበር። ከላይ በታምራት ላይኔ – ከታች በእኛ። መካከሉ ላይ ተጨፍልቆ ምንም ስራ መስራት አይችልም ነበር። ዲማ ደህና ነው። አላረጀም። ጥቂት አወራን። ፎቶም ተነሳን።

ሙሉነህ እዮኤልን ሳየው ግን ግራ ገባኝ።

“ግንቦት 7ን ወክለህ ነው ወይስ በግል?” ስል ጠየቅሁት።

“በግል” ሲል መለሰ።

 የአሰፋ ጃለታ ወረቀት ትኩረቴን ከሳቡት መካከል አንዱ ነበር። “The Impact of colonialism on Oromo Institution”በሚል ርእስ ጠቃሚ ነገር አቀረበ።

የOSA ኮንፈረንስ በአጀንዳው የኢትዮ-ኦሮሚያን ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት የሚዳስስ፣ መጪውን ዘመን የሚጠቁም የፖለቲካ ትንበያ ባያክልም በጥቅሉ ጥሩ ነበር። አንድ የማይካድ እውነት አለ። የኦሮሞ ህዝብ ለአንድ ግብ የኤሊ ጉዞውን ተያይዞታል። በርግጥ ግቡ ላይ ሳይደርስ ዘግይቷል። መድረሱ ግን አይቀርም። ይህን መጠራጠር አይቻልም። እየተሰዋ፣ መሬት እየቆነጠጠ ወደፊት እየገፋ ነው። በፖለቲካ አመለካከት፣ በጎሳና በሃይማኖት ጎራ የመለያየትና የመደራጀት ዝንባሌዎች (በዳያስጶራ) ቢታዩም ምሁራኑና የፖለቲካ ሳይንቲስቶቹ የኦሮሞ ህዝብ መጪ ዘመን ላይ ባላቸው ህልም ዞሮ ዞሮ ልዩነት ያላቸው አይመስልም።

Source: http://tgindex.blogspot.ch/2017/07/osa.html?spref=fb&m=1

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s