የፋይናንስ ገቢ፣ ግብርና ታክስ!!


አንቀፅ 98(2)

በድርጅቶች የንግድ ትርፍና የባለ አክሲዮኖች የትርፍ ድርሻ ግብርና ታክስ በጋራ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ።

አንቀፅ 98(3)

በከፍተኛ ማዕድን ግብርና ታክስ በጋራ ይጥላሉ፣ ይሰበስባሉ። (መካከለኛና አነስተኛ ማዕድን ሥራ የክልሎች መሆኑ ሌላ ቦታ ተገልፆዋል)

አንቀፅ 100(1)

ክልሎችና ፌዴራል መንግሥት ግብርና ታክስ በሚጥሉበት ጊዜ ከምንጩ ጋር የተያያዘ መሆኑ በጥንቃቄ ማጥናት አለባቸው። (የገቢው ምንጭ ለማለት ነው)

አንቀፅ 100(3)

ለትርፍ የቆመ ካልሆነ በስተቀር ክልሎች በፌዴራል መንግሥት ንብረት ላይ ግብር የማስከፈል ስልጣን አይኖራቸውም። (ለትርፍ የቆመ ከሆነ ግብር ማስከፈል ይችላሉ)

ኦህዴድ ይህን ሁሉ ተኝታበት አሁን ታለቃቅሳለች።

ሌሎች ክልሎች የማይናገሩበት ምክንያት አላቸው። ከኦሮሚያ የሚሰበሰበው ግብር በፌዴራል በኩል ስለሚደርሳቸው መናገር አይፈልጉም።

ኦህዴድና የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አሁን ልቅሶ አቁመው በነዚህ ህገ መንግሥታዊ አንቀፆች እንቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው።

የግል ድርጅቶች እነ ማን ናቸው? እነ ዳንጎቴ ሲሚንቶ፣ እነ ደርባ ሲሚንቶ፣ እነ ሜድሮክ፣ እነ ሆራይዘን ፕላንቴሽን፣ እነ ሀበሻ ሲሚንቶ፣ ኦሮሚያ ውስጥ የተተከሉ ቢራ ፋብሪካዎች በሙሉ፣ ኦሮሚያ ውስጥ ያሉ የአበባ እርሻዎች በሙሉ፣ ኦሮሚያ ውስጥ የተተከሉ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች በሙሉ፣ ኦሮሚያ ውስጥ የተተከሉ የፕላስቲክ ፋብርካዎች በሙሉ፣ ኦሮሚያ ውስጥ የተተከሉ የብረታ ብረት ፋብሪካዎች በሙሉ፣ ኦሮሚያ ውስጥ የተተከሉ የውሃና የማዕድን ውሃ አምራቾች በሙሉ፣ ኦሮሚያ ውስጥ ቅርጫፍ የከፈቱ የንግድ ባንኮችና ኢንሹራንሶች በሙሉ እና ሌሎች ያልተጠቀሱ። እስካሁን ከህገ መንግሥት ውጭ የፌዴራል መንግሥት በህገ ወጥ ለ26 ዓመታት ብቻውን ግብር ሲሰበስብ ነበር። ለ26 ዓመታት ከሰበሰበው ውስጥ 50% የኦሮሚያን ድርሻ ከነወለዱ መመለስ አለበት።

ከዚህ አመት ጀምሮ 50% በህገ መንግሥቱ መሠረት ለኦሮሚያ መከፈል አለባቸው። እነዚህ ድርጅቶች ዋና ምዝገባቸው የትም ይሁን የት ከጋራ ግብርና ታክስ ማምለጥ አይችሉም። ኦህዴዶች በዚህ ልሸውዱን አይችሉም።

ለትርፍ የተቋቋሙ የፌዴራል መንግሥት ንብረት እነ ማን ናቸው? ኦሮሚያ ውስጥ የተተከሉ የስኳር ፋብሪካዎች በሙሉ፣ ሙገር ሲሚንቶ እና ሌሎች ወደ ግል ያልዞሩ የመንግሥት ድርጅቶች ላይ የኦሮሚያ መንግሥት ግብርና ታክስ የመጣል ስልጣን አለው።

ኦህዴዶች ለቅሶ አቁማችሁ በዚህ ዓመት ይህንን መፈፀም ይጠበቅባቸዋል።