​Dr Berhanemeskel Abebe Segni: የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎቹን በOPDO  መስቀማት የለበትም። 

የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎቹን በOPDO  መስቀማት የለበትም። 

****************************************

ታላቁ የኦሮሞ ህዝብ  ቅዎሜ(#OromoProtests) ከተጀመረ ሁለት ዓመታት ልሆኑት ጥቂት ወራት ይቀሩታል።  

ለቅዎሜው መነሻ የሆኑት የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎች ግን እስከ ዛሬ አንዳቸውም ምላሽ አላገኙም። 

ላለፉት 25 ዓመታት የተዘረፈው የኦሮሞ ህዝብ መሬት አልተመለሰም። ከዚህም በኃላ ዝርፊያውን ለማስቆም የዛረፋ ህጎቹን ሽሮ የህዝቡን የመሬት ባለቤትነት የሚያረጋግጡ ህጎችና ፓሊስዎች ማውጣት ቀርቶ የተሰበም የለም። 

ኦሮሚኛ ከአማርኛ ጎን ለጎን በእኩል ደረጃ የፌድራል መንግስቱ የሥራ ቋንቋ አልሆነም። ይህን ለኢትዮጵያ ህዝቦች የግንኙነት ድልድይ እና የአንድነት መርከብ የሚሆንን ትልቅ ነገር ስራ ላይ ማዎል ቀርቶ ሥራውን ለመጀመር  የፓሊስ ሃሳብ  የሚያቀርብ የባለሙያዎች አካል እንኳን ተለይቶ አልተቋቋመም። መታሰቡንም እጠራጠራለሁ። 

አድስ አበባ፣ ድሬደዋና ሀረር ከውስጡ ከተለዩት ህዝብና አገራቸው በኦሮሚያ ስር ተመልሰው እንደቀድሟቸው የኮሩና የደሩ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ፣ የባህልና የፓላቲካ መዕከል አልሆኑም። ይህ ባለመሆኑ  ከ1991 በፊት የኢትዮጵያ ዝነኛ የፍቅርና የአንድነት ከተማ የነበሩት ሀረርና ድሬደዋ በተሸረበባቸው ሴራ አስታዎሽ አጥተው እየጠፉ ነው። ህዝባችንም ከተማ አልባ ህዝብ ሆኗል። 

የኦሮሞ ህዝብ በቀዬው በኦሮሚያ አባ ወራ፣ በአገሩ በኢትዮጵያ ላይ በለአገር አልሆነም። 

ይባስ ብለው እነዚህን የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎችን  ያነሱትን የኦሮሞ ህዝብ መሪዎችና ልጆች አስረዋል። ከእስር ቤትም አልተፈቱም። 

እየሆነ ያለው ነገር አስደንጋጭ ነው። የኦሮሞ ህዝብ ምንም ምላሽ ሳያገኝ ጩኸቱን ተቀምቷል። 

መጀመሪያ ኦነግና ግንቦት ሰባት ከየትኛውም የፓለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገነውን የህዝባችንን ትግል ቀምተው ሊሳፈሩት ዳድተው ነበር። ያ በኦሮሞ ወጣቶች ብርቱ ትግልና ጥረት አልሆነም። 

አሁን ግን የህዝቡ ትግልና ጥያቄ በOPDO የተቀማ ይመስላል።  የኦሮሞ ወጣቶች ወይ እየሆነ ያለውን አላስተዎሉም፣ ወይም የሞቱና የታሰሩ ወንድሞቻቸውን እና እህቶቻቸውን ረስተው ቡኩርናውን ለአንድ ምስር ወጥ ለያቆብ እንደ ሸጠው ኤሳው ሆነዎል። አስደንጋጭ ነው። 

ትናንት ደክተር መረራን በፈረስ ወጥቶ የተቀለው ህዝብ እሱን እና ሌሎች በሽዎች የሚቆጠሩ የህዝባቸውን ጥያቄ የነገቡትን ልጆቹን ፍቱ ብሎ እንደመጠየቅ አሳሪውን መንግስት የሚወክለውን ለማ መገርሳን አጨብጭቦ ይቀበላል። 

አይ ኦሮሚያ አይደለም ያሰራቸው የፌድራል መንግስቱ ነው የሚል ከለ፣ ቀኝ እጄ የሚሰራውን ግራ እጄ አያውቅም የሚልን ጅል መሆን ነው። የኦሮሞ ልጆችን ደህንነት ከላስጠበቀ ለማ ምኑን የአሮሞ ፕረዝደንት ሆነ ታዲያ? የመጀመርያ ተግባሩ እነዚህን ውድ የኦሮሞ ልጆች መስፈታትና ደህንነታቸውን መጠበቅ አይደለም?  ህዝቡም ይህ እንዲደረግ ማስገደድ አለበት።

ህዝቡ የኦሮሚያና የፌድራል  መንግስቱን አስገድዶ የሱን ጥያቄዎች በማንሳታቸው ብቻ የታሰሩት መሪዎቹን  ከላስፈታ፣ ለሞቱት ልጆቹ ካሳ ከላስከፈለ፣ ልጆቹንና መሪዎቹን የገደለውና ያሰረው ራሱ የኦሮሞ ህዝብ ነው። ህዝቡ ከደር እስከ ደር መክሮና ዛክሮ መንግስት በሰላማዊ መንገድ ልጆቹን ማስፋታትና የህዝቡን ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ በመንግስት ለተገደሉት መታሰብያ ማስቆም  እስካልቻለ ድረስ ነገ ለርሱ የሚሞት ጀግና እና ለርሱ የሚናገር መሪ እንደማያገኝ መገንዘብ አለበት።   

ነግ በኔ ነውና ለትናንት መሪዎቹ የኦሮሞ ህዝብ ዛሬ በነቂስ ወጥቶ ከልቆመ ለማ መገርሳ እራሱ በልቡ እንሚያዝንባችው እወቁ።ለማ መገርሳ እራሱ ትናንት ለኦሮሞ ህዝብ ከቆሙት ከነደክተር መረራንና ሌሎች መሪዎቹ ጋር ህዝቡ ያልቆሙን ሲያይ፣ በተለይ ከልቡ ከሆነ ለህዝብ የሚሰራው፣ ነገ ራሱ በባዕድ ብጠቃ ደምመላሽ ወገን አለኝ ብሎ እንበደማይታመንባችው እያንዳንዱ ኦሮሞ በግልም በቡድንም መገንዘብ አለበት። 

የለም ፕረዝደንት ለማ ህግና መመሪያ ሳያወጣ በቃሉና በንግግሩ ብቻ ከተወሰደው ብዙ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ነገ ተመልሶ ያለመወሰዱን ምንም አይነት ህጋዊ መተማመኛ ያሌለው ሁለት ጥመድ የአባቴ መሬት መልሶልኛል ብሎ በባዶ ሜዳ መፈንደቁ ሰዋችን ማያት ያሳዝናል። ከንቱ የምርቃና ፓላቲካ። 

 OPDO መመሪያ ሳይቀርፀ፣ ህግ ሳያወጣ፣ OPDO ራሱ ትክክለኛና ህጋዊ የህዝብ ጥያቄዎች ናቸውና እመልስለሰቸዎለሁ የሚላቸውን ጥያቄዎች ያነሱትን የኦሮሞ መሪዎችና ውድ ልጆችን ከእስር ሳይ ፈታ፣ ለሞቱት ጀግና የህዝብ ልጆች ካሳ ሳይከፉልና መታሰብያ ሃውልት በየከተማው ሳያቆምላቸው፣ የህዝብን ጭኸት ለመቀምት የተጀመረውን የማጃጃል ፓለቲካን ህዝቡ የጥያቄዎቹን ከፓለቲካ ድርጅቶች ገለልተኛነት ጠብቆ በህግና በተቋም የፀና ምላሽ ለማግኘት ትግሉን እጁ መመለስ አለበት።  

ልጆችህን እየገደለ፣ እያሰረ፣ ከአገር እያወጣ ፣ ወራሽ ልጆች እያሳጣህ፣ አለማሃሁ፣ በለአገር አደርግሃለሁ የሚል የማጃጃል ፓለቲካ ህዝባችን በለአገር እያደረገ ሳይሆን እየገደለና በቁም እየቀበረ መሆኑን የኦሮሞ ህዝብና የኦሮሞ ወጣት አሁኑኑ ይህ ችግር ሌላ የባሰ ችግር ሳይወልድ፣ ሳይውል፣ ሳያድር፣ የነገሩን አከሄድ በጥልቀት በመመርመርና በመገንዘብ የህዝባችን ጥያቄ ስርነቀልና ዘላቂ መፉትሄ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s