ወቅቱን በማስመልከት ከ ተበዳይነሽ ለ በዳይነሽ የተፃፈ አጭር መልዕክት!

Via Abba Joel on Facebook

እህቴ ሆይ፣ እኔ ቤት የተለኮሰ እሳት ካንቺ ጓዳ የማይደርስ ከመሰለሽ ተሳስተሻል። ሰለባዎቹ ሁለታችንም ነን። ይህን አትጠራጠሪ። በልጅሽ የተለኮሰው እሳት መጥፋት ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል። ዝምታሽ ግን አልገባኝም። ልጅሽ ይህን ድርጊት ሲፈፅም በዝምታ መመልከትሽ መልካምም አይደል። በለው እንደማለት ይቆጠራል። ልጅሽ ልጄን በገደለ ማግስት አብረሽኝ ሃዘን በመቀመጥ ፈንታ ዳንኪራ ትረግጭ ነበር። ትላንት ተበደልኩ ብለሽ አሻፈረኝ እንዳላልሽ ዛሬ ልጅሽ ልጄን ሲበድለው በዝምታ መመልከትሽ ለበጎም አይደል። ከማወራው በላይ የሚፈፀመውን አይንሽ እያየ ጆሮሽም እየሰማ ነው። ስለዚህ ብዙ አላድክምሽ። አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሆኜ ልንገርሽ። ልጅሽ የለኮሰው እሳት ወደ ሰደድ እሳትነት ተቀይሯል። ለጊዜው ሰለባ የሆኑት የኔ ልጆች ናቸው። የነገው ጥፋት ግን በኔም ባንቺም የከፋ ወደመሆኑ ተቃርቧል። ስለዚህ እህቴ በአስራአንደኛው ሰዓትም ቢሆን ዝምታሽ ተሰብሮ ልጅሽን ተው ማለቱ ለኔም ላንቺም ይበጃልና ደግመሽ ደጋግመሽ አስቢበት። 

ተበዳይዋ እህትሽ!

• እንደው በዚህ መልክ እንኳን ከገባቸው