የዛሬ 15 ቀን “በክልሎች መካከል አስተዳደራዊ ወሰን የማካለል ችግርና የኦሮሚያ ክልል አዲሱ ተሞክሮ” በሚል ርእሰ ኣንቀጽ ሪፖርተር ድህረ ገጽ ላይ እንዲህ ተብሎ ነበር! ኦሮሚያን እንደቅርጫ ሊከፋፈሉዋትና ሊሸጡዋት የሚመኙ የወያኔ መሪዎች እንዲህ ይላሉ

////

“በኢትዮጵያ ውስጥ ከአንድ ዓመት በፊት ተከስቶ ለነበረው ሁከትና ብጥብጥ እንደ መነሻ ምክንያት ከተወሰዱ ጉዳዮች አንዱ በክልሎች መካከል ያለው አስተዳደራዊ ወሰን ያልተካለለ በመሆኑና ከዚህ ጋር ተያይዘው በመጡ ሌሎች ጉዳዮች እንደነበር ማስታወስ ይቻላል፡፡”

////

“ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል ተፈጥሮ የነበረው ብጥብጥ ለወራት የቀጠለና በኋላ ላይም መሠረቱን አስፍቶ አገራዊ ቀውስ አስከትሎ እንዳለፈ አይዘነጋም፡፡ የአዲስ አበባ ከተማን ለማስፋፋት በተደረገው እንቅስቃሴ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ጋር ያላት አስተዳደራዊ ወሰን እንደተካለለ መረጃዎች ቢጠቁሙም፣ ከተማዋን ወደ ጎን ለማስፋፋት በተደረገው ሙከራ በሕዝቡ ዘንድ ተቃውሞ በማስነሳቱ ውጤታማ ሳይሆን መቅረቱ ይታወቃል፡፡”

////

“ከዚህም በተጨማሪ አዲስ አበባ በአብዛኛው ከኦሮሚያ ክልል ጋር የምትዋሰን በመሆኑ፣ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ልታገኝ የሚገባው ጥቅም መረጋገጥ እንዳለበት ለብዙ ጊዜ በክልሉ ተወላጆች ሲጠየቅ ቆይቷል፡፡ ጥያቄው ከቀረበ ብዙ ዓመት ቢያስቆጥርም ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር ባካሄዱት ውይይት፣ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ልታገኝ ስለሚገባት ጥቅም በሚመለከት በሚቀጥለው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚፀድቅ ተናግረዋል፡፡”

////

“አዲሱ የክልሉ ካቢኔ የ2009 ዋነኛ ዕቅዱ ኦሮሚያን በሚያዋስኑ ክልሎች መካከል ያለውን አስተዳደራዊ ወሰን በግልጽ መለየት ነው፡፡ በክልሉ ብሎም በአዋሳኝ ድንበሮች መካከል የሚኖሩ ዜጎች ዋስትናቸውን ማረጋገጥ እንደሆነም ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡”

////

ከአማራ ክልል ጋር ያለውን አስተዳደራዊ የወሰን ችግር ለመፍታት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ኃላፊነቱን ወስዶ በመንቀሳቀስ ላይ እንዳለ የሚናገሩት ባለሥልጣኑ፣ በቀሪዎቹ ሦስት ወራትም ችግሮችን ሙሉ በሙሉ እንደሚፈታ ገልጸዋል፡፡”

****

ምንጭ:  ሪፖርተር ጋዜጣ