​ከአለም አቀፍ የዋቄፈና ጉባኤ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ከአለም አቀፍ የዋቄፈና ጉባኤ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ቀን 05.06.2017 እ.አ.አ

ጉዳዩ ፕሮፌት ሱራፌል ደምሴ ሜይ 30 ቀን 2017 የተለቀቀ እሬቻንና ዋቄፈና እምነትን የሚያንቋሽሽ ቪዲዮን ይመለከታል

የአለም አቀፍ የዋቄፈና ጉባኤ በፕሮፌት ሱራፌል ደምሴ ሜይ 30 ቀን 2017 የተቀቀን ዋቄፈናንና እሬቻን የሚያጠለሽ ቪዲዮ በተለያዩ ሜዲያዎች (youtube, facebook, TV channel) እና በድህረ ገጻቸው ላይ ስንመለከት እጅግ ሀዘን ተሰምቶናል https://www.youtube.com/watch?v=rX1p6rOY_7c) ።

ስለእግዝሃብሄር የሚሰብክ አንድ ፕሮፌት የኦሮሞን ህዝብ ታሪክ፣ ማንነትና እምነት ሲያጥላሉ ስንመለከት ማመን አቃተን።

እሬቻ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችና ሌሎችም ህዝቦች በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በተለይ በሆረ አርሰዴ / ቢሾፍቱ ለብዙ አመታት ሲያከብር የኖረና ያለ መሆኑ አይካድም። በዛሬው ጊዜ በተለይ ለኦሮሞ ህዝብ እሬቻ እንደ አገር አቀፍ በዓል እየተወሰደ ነው። የትኛውም እምነት ያለው ኦሮሞ እንዲሁም ሌሎችም ህዝቦች ብዙ ቱሪስቶችን ጨምሮ የሚሳተፉበት ትልቅ አለም አቀፍ በአል ሆኗል። እሬቻ የአንድ እምነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኦሮሞች ማንነት መገለጫ ነው።

ዋቄፈና እምነት ደግሞ ከብዙ ሺዎች አመታት ጀምሮ የኦሮሞ ህዝብ የራሱን ዋቃ ስያምን የኖረበት እምነት ነው። ዋቄፈና በወንዝ፣ በጋራና በጣኦት የሚያመልክ እምነት አይደለም። ዋቄፋና በኦሮሞ ዋቃ ጉራቻ ብቻ የሚያምን ራሱን የቻለ የኦሮሞ ህዝብ የጥንትና የዛሬም እምነት ነው። የኦሮሞ ህዝብ የተለያዩ እምነት ያለው ህዝብ ሲሆን ለአመታት ከራሱም ሆነ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተከባብሮ የኖረ ህዝብ ነው።

ነገር ግን ፕሮፌት ሱራፌል ደምሴ በሜይ 30 ቀን 2017 በለቀቁት ቪድዮ ላይ እሬቻንና ዋቀፋናን ሲያቋሽሹና ስያጥላሉ ተስተውለዋል። ይህ ደግሞ በህዝቦች መሃል ያለውን ተከባብሮ መኖር መንፈስ የሚያደፈርስ ነው። በኦሮሞ ህዝብም ሆነ በሌሎች ሰላም ወዳድ ህዝቦች ተቀባይነትም አይኖረውም።

የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላም የመፍታት ባህል ያለው፣ የሌሎችንም ህዝብ እምነትና ባህል አክባሪ ህዝብ ነው።

ለዚህም አለም አቀፍ የዋቄፈና ጉባኤ ፕሮፌት ሱራፌል ደምሴ የኦሮሞ ህዝብን ይቅርታ እንዲጠይቁና ይህንን ጠብ አጫሪ ቪድዮ ከሁሉም ሚዲያ ላይ በአስቸኳይ እንዲያነሱት እንጠይቃለን።

ይህ የተሳሳት አመለካከት በሰላማዊ ህዝቦች መካከል ሊፈጠር ችግር ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑንም ከወዲሁ እናሳስባለን።
አለም አቀፍ የዋቄፈና ጉባኤ

ግልባጭ

ለኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ጽ/ ቤት፤ ለክቡር አቶ ሙላቱ ተሾመ

ለጠ/ሚንስትር ቢሮ፤ ለክቡር አቶ ሀይለ ማሪያም ደሳለኝ

ለጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት፤ ለክቡር አቶ ለማ መገርሳ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s