​ጠቅላይ ሚንስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ የሀብት ምንጫቸውን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚንስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ የሀብት ምንጫቸውን ገለፁ።

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ የመንግስትን የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንደገለጹት በመንግስት ኃላፊነታቸው ከሚያገኙት ገቢ በተጨማሪ በቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ እና በጋምቤላ ክልሎች እየተዘዋወሩ ወርቅ እንደሚያመርቱ ተናግረዋል። 
ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሄ የኔ ነው የሚሉት ነገር እንዴት ነው የሚገኘው የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ይቀርብላቸው እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚንስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለጥያቄው ሲመልሱ 
“ይሄ የሚገኝበት መንገድ በተግባር በሚገባ ተረጋግጧል። እንደሚታወቀው ትግራይ ክልል፣ ቤንሻንጉል ክልል፣ ኦሮሚያ ክልል፣ ጋምቤላ  እና ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልሎች ሰፊ የወርቅ ምርት አላቸው። ስለዚህ መነሻ ገንዘብ ማምጣት የፈለገ ሰው ሰፌድ ይዞ ሄዶ ወርቁን አንጥሮ ብር ማምጣት ይችላል። እኔም ከዚህ የተለየ አላደረግኩም።” ብለዋል።
የጠቅላይ ምንስትሩን  የስራ ፈጠራ እና ኢንተርፕሩነርሺፕ ክህሎት በማስመልከት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተያየታቸው የሰጡ ሲሆን በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ዩኒቨርሲቲ የማዕድን እና ኢነርጂ ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ገብረወርቅ ኪዳነ ይገኘበታል። 
ገብረወርቅ እንደተናገረው “ጠቅላይ ሚንስትሩ ከመንግስት ኃላፊነታቸው በተጨማሪ በአነስተኛ እና ጥቃቅን የወርቅ ማምረት ሥራ መሳተፋቸው ለሁላችንም ትምህርት ሊሆን ይገባል።ወርቅ ማምረት በጣም ቀላል ሥራ ነው። የሚይስፈልገው ግብአት አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት ቤንሻንጉል ክልል ሰፌድ ይዞ ሄዶ ወርቅ አምርቶ መመለስ እንደሚቻል በጥናት አረጋግጠናል።” ብሏል። 
ከዚህ ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡ የጠቅላይ ሚንስቴሩን አርአያነት በመከተል ወርቅ የማምረት ፍላጎቱ የጨመረ ሲሆን በመርካቶ ሰፌድ ተራ ከሰፌድ ፍላጎት እና አቅርቦት አለመመጣጠን ጋር ተያይዞ የሰፌድ ዋጋ አሻቅቧል። 
ቅዳሜ ለት በዋለ የሰፌድ ዋጋ አነስተኛ ሰፌድ በ አምስት ሺህ ብር ሲሸጥ መካከለኛ እና ሰፋፊ ሰፌዶች እስከ አስራ አምስት ሺህ ብር ተሽጠዋል። ከዚህ በፊት እንጀራ በመጋገር ሙያ ተሰማርተው የነበሩ የከተማዋ ነዋሪዎችም ሰፌዳቸውን ወደወርቅ ማምረቻነት ለመቀየር እየወሰኑ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።    
ጠቅላይ ሚንስትሩ በሌላ በኩል ባለፈው አመት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋትና ተጨማሪ ግንባታዎችን የማካሄድ ስራ ተጠናክሮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል። በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የሙያ ደረጃና ብቃት ምዘና፣ በአሰልጣኞች ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ፣ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር የተለየ ስራ ተሰርቷል ሲሉ አክለዋል።  
ሪፖርተር – ስታፍ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s