​”””””””” እኛኮ……””””””

“””””””” እኛኮ……””””””

እኛኮ 

ምን አለብን ረኮ?

ከቤታችን ያለ ያንተ ወንድም ምርኮ 

ያንተን እግር ታኮ 

ከራስህ አስታኮ 

ስጋህን አኝኮ 

እፊትህ ላይ መትፋት

ይቻላል ሺ መግፋት 

ሺ መድፋት 

እኛኮ 

ምን አለብን ረኮ ?

በቂም ብንነሳ በጥቀርሻ እይታ 

በጥበት ሁካታ

ከንባችን ዘላላ ያንተን ሲቃ ዋይታ 

ስቃይህን መቅዳት 

ይቻላል ሺ መጉዳት 

እኛኮ 

ምን አለብን ረኮ 

ባንተ በደል ሴራ እያንዳንዱን አንቆ 

ሲሆን አስጨንቆ 

መደርመስ ነቅንቆ 

መጣል፣ከአፈር አደባልቆ 

መሰረትክን ንዶ 

ማጋየት አንድዶ 

እኛኮ 

ምን አለብን ረኮ 

የቅልናህ መንገድ የጅህልናህ በሩ 

ስልጡን አይምሮዋችን እንቢ ሲለን ቅሩ 

መሞትን ሳንፈራ አልከን መግደል ፈሩ 

ሲለቃቀሙብን ልጆቻችን ከስር 

ተስፋችን ሲከስር ያለ ፍትህ እስር 

የማያንገበግብ የማያቃጥለን 

ጎዳና ስንወድቅ ስንሞት ተነጥለን 

ለምን የማያመን?

እኛኮ 

ብዙ የኛ ረኮ 

መች ሳያመን ቀርቶ 

የማይቆጨን ሞቶ 

የግብዣህ ወረቀት ጥሪው ተስተጋብቶ 

አላምን ብንል እንጅ ከልባችን ገብቶ 

መቼ ያውቀን እና ፍርሀት እኛን ከቶ 

እኛም ባቅማችን አንተም በጉልበትህ 

እንግዲ ተሳክቷል ምኞት ፍላጎትህ 

እኛኮ 

የሰላም ተልኮ 

ከሰንህ በገሀድ ምስክር አቁመን 

የደረሰብንን ችግር ጠቁመን 

ብንናገር 

ነውር ባንተ ሀገር 

እብሪትን የሸሸ ፈሪና ገራገር 

ሀሞት ወኔ የሌለው 

ስሜት የጎደለው 

ተወሽቆ ስሬ በለው በለው 

ሲለኝ እየሰማው 

ያንተን ስጋ ዘመድ በጥፊ ማልመታ ይህ የኔ ዝምታ 

አልሆነም ውለታ 

እኛኮ 

እንቢ ብንል ጥልን 

በቂም መነጠልን 

መፈራካከስ መገነጣጠልን 

ማፍረስ ማቃጠልን 

ጠልተን ብናወገዝ 

የድንፋታህ መዘዝ 

በአጥንት ተደላድሎ በደሙ በርክቷል 

ሊገል የቆረጠው ከሞተው በርክቷል !!

        ቢሊሱማ ቢሊሱማ ( 1/8/2016)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s