​#Irreecha 2016: Ibsa KFO ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ/ኦፌኮ የተሰጠ መግለጫ

#Irreecha 2016: Ibsa KFO

ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ/ኦፌኮ የተሰጠ መግለጫ

የኢሬቻ በዓል ለኦሮሞ ሕዝብ ልዩ ትርጉም አለዉ፡፡ በተለይ የክረምቱ ዝናባዊ ወቅት አልፎ ወደብራ በመሸጋገራችን የኩሽ ሕዝቦች በአጠቃላይና በተለይ የኦሮሞ ሕዝብ ወደ መልካ (ወንዝ) ወርዶና ወደ ቱሉ (ተራራ ወይም ኮረብታ) ወጥቶ ዋቃን (እግዚአብሔርን) እያመሰገነ የሚያከብር ነዉ፡፡ በአጠቃላይም የኢሬቻ በዓል በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ አንድም ሃይማኖታዊ ነዉ፤ ሁለትም ባህላዊ ነዉ፡፡ ሃይማኖታዊም ሆነ ባህላዊ አከባበሩ የዚያ የሚያራምደዉ ሕዝብ ታሪካዊ አንጡራ ሀብትና መገለጫ ነዉ፡፡

እንደሚታወቀዉ የኦሮሞ ሕዝብ እምነት፣ ባህልና ታሪክ ለረጅም ዓመታት በተፅዕኖ ሥር ከቆየ በኋላ ዛሬም አስተማማኝነቱ ባይረጋገጥም በሕዝብ ልጆች መስዋዕትነት ወደ ነበረበት ቦታዉ እየተመለሰ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ ማንነት መገለጫ የሆነዉ የኢሬቻ በዓል ከስሙ ዉጭ ባዕድ ስም እየተሰጠዉ ሲጣጣል ከቆየ በኋላ የበዓሉን ወግና ሥርአት በያዘ ሁኔታ መከበር ቢጀምርም፤ ዛሬም ድረስ ራሳቸዉን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በተለያየ ስም የጫኑና ለመጫን የሚፈልጉ ኃይሎች የበዓሉ አከባበር ከሚጠይቀዉ አግባብ ዉጭ በዋዜማዉ የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ፣ እንደዚያ ዓይነት ልብስ ልበሱ፣ እንደዚያ ዓይነት ጨርቅ ያዙ፣ እንደዚያ ዓይነቱን ምልክት አትያዙ እየተባለ የፖለቲካም ሆነ የግል ፍላጎታቸዉን በሕዝብ ላይ ለመጫን እየሞከሩ ከመሆናቸዉም በላይ፤ በሌላ በኩል ደግሞ እየቀጨጨ የነበረዉን የአገራችንን ዲሞክራሲ መቃነ መቃብር መፈፀም ይሆናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢሬቻ የባህልና የምስጋና ቀን መሆኑ እየታወቀ የበዓሉ አከባበር ከሚጠይቀዉ ሥርአት ዉጭ በመልካ መዉረጃዉ መንገድ ላይ የኪነት ቡድን አደራጀቶ ማስጨፈር፣ የፖለቲካ ሰዎች እየተቀባበሉ የፖለቲካ ንግግር ማድረግ፣ መንገድ በማጣበብ አማኞችና ምስጋና አቅራቢዎችን ለሌብነትና እርስ በርስ ለመረጋገጥ ማጋለጥ ከቀድሞዉም ጀምሮ ያልተገቡ ድርጊቶች ናቸዉ፡፡ ማንም አካል የፖለቲካ ሥራዉን ቢሰራ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ የሚቀበለዉ ቢሆንም በሕዝብ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ክብረ በዓል ቦታዎች ላይ ባይሆን እንመርጣለን፡፡

የ2009 የኢሬቻ በዓል ከምንጊዜዉም በላይ ሠላማዊና ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሚሣተፉበት በዓል እንዲሆን የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ይፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ ያለምክንያት አይደለም፡፡ በ2008 እና ከዚያም ቀደም ብሎ የኦሮሞ፣ የወልቃይት ጠገዴ፣ የቅማንት፣ የኮንሶና የጋምቤላ ሕዝብ ባነሳዉ የመብትና የማንነት ሠላማዊና ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሕዝብ ልጆች በተለይም በኦሮሚያ፣ በአማራና በደቡብ ብሔር፣ ብህረሰብና ሕዝቦች ክልሎች ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ተሰደዋልም፡፡ እንግዲህ ይህንን ግምት ዉስጥ በማስገባት ከመላዉ አገሪቱ ወደ በዓሉ የሚመጡ ታዳሚዎች ይህንን በዓል በፀሎት፣ በመዝሙርና በዝምታ ማሰብ ስለሚጠበቅባቸዉ ነዉ፡፡ አባቶችና የመስኩ ባለሙያዎች ትምህርት ይሰጣሉ፡፡ ከዚህ ዉጭ ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ በበዓሉ ሥፍራም ሆነ አከባቢዉ ላይ (ለሕይወት ከሚያስፈልገዉ ምግብና ዉሃ በስተቀር) የፖለቲካም ሆነ የዳንክራ ሥፍራ እንዳይሆን እንመክራለን፡፡ በመጨረሻም በዓሉን በማስተባበርና ፀጥታ በማስከበር ሥራ ላይ የተሰማሩ አባላትና አካላት ለሕዝብ ፍቅር በማሳየት በዓሉ እንዲከበር እንደሚያደርጉ እናምናለን፡፡ ታዳሚዎችም መብታቸዉና ፍላጎታቸዉ እንዲከበርላቸዉ የሚፈልጉትን ያህል ሥርአትን ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን የኢሬቻ በዓል የሕዝብ ባህልና ሃይማኖት በጣምራ የሚከበሩበት መሆኑ ታዉቆ፤ ማንናቸዉም የፖለቲካ ኃይሎች ከዋዜማዉ ጀምረዉ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ አበክረን እናሳስባለን፡፡

መልካም የኢሬቻ በዓል እንዲሆን እንመኛለን!

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ

መስከረም 10/2009

ፊንፊኔ

Via Nagessa Oddo Dube

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s