​”ዲሬ ኡልፎ!”

​”ዲሬ ኡልፎ!”

   Source: @Dr Tsegaye Ararssa’s Facebook page  

========

ከዕለታት ባንዱ ቀን በቀነ ጎደሎ 

ሰኔና ሰኞ ተገጣጥሞ ውሎ

በጠዋት ተነስታ ቡና አፍልታ እናቴ

ማልዳ ልትማፀን የናቷን አቴቴ

አባት አባ ወራ ከእንቅልፉ ሳይነቃ

ፀሎትም ሳያደርስ ምስጋና ለዋቃ

የማለዳ ጮራ ጀንበር ስትፈነጥቅ

ካኪ የለበሰ አንድ ባለ ሙሉ ትጥቅ 

እናትና አባቴን እደጅ ጠርቷቸው

ጆሮ ‘ሚያደነቁር መርዶ አረዳቸው

“ያላችሁባት መሬት 

የመንግስት ሀብት ናት

እናንተም ተነሱ

ቤቱንም አፍርሱ

ተነሱ!…ተነሱ!…

አንዳች አትተንፍሱ!

አንዳች አትመልሱ!”

ይህንን ሲሰማ..

“እትብቴስ! እትብቴ! እትብቴ!”

ብሎ ጮኸ አባቴ

“እትብታችን የተቀበረባት

ያያት የቅድማያት አፅም ያረፈባት

የዋቄፈና ምድር የኢሬቻ 

ለፈጣሪ ውለታ ገለታ ገልቻ

ለዲሬያችን አያና

የምንሰጥባት ምስጋና 

ያለንባት መሬት 

‘ዲሬ ኡልፎ’ ቅድስት ናት”

ታጣቂው ትዕቢቱ

የንቀት ብዛቱ

ቃላቱ ክርፋቱ

“እትብትህን ቆፍረን ካረፈበት ቦታ

እንልክልሃለን አሽገን በፖስታ

ያንተን ኢሬቻ ኡልፎ ኮተታ ኮተት

ጠቅልለሃቸው ሂድ ወደ ምትሄድበት”

እኔ! ያባቴ ልጅ ቄሮ 

አልችል በደል እሮሮ

ንቀት አበረረኝ 

እንደ እብድ አደረገኝ

ሆኘ ውርደት ከልካይ ያባቴ መከታ

ቆሚያለሁ ከፊቱ ከታጣቂው ሽፍታ

እስቲ ንክች!

አልል ፍንክች!

ይጉረፍ ደሜ ይከስከስ አጥንቴ

አይፈርስም ቤታችን የናቴ ያባቴ

ከተቀበረበት አይወጣም እትብቴ

“ዲሬ ኡልፎ” አትደፈር

ልሙትላት ልሁን አፈር።

       =///=

                                        –M.T., 19/08/16

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s