​የጀልዱ ህዝብና ካቢኔዎቹ (ኢጆሌ ጀልዱ)

የጀልዱ ህዝብና ካቢኔዎቹ

(ኢጆሌ ጀልዱ) @Facebook

ደፋር ብዙ ቦታ አለ፡፡ ግን እንደ ጀልዱ ህዝብ ደፋር አላየሁም፡፡ ፍቅራዊ ድፍረት፡፡ ጥይት ሳይፈራ በማጭድና ማረሻ ለነፃነቱ የሚፋለም ህዝብ፡፡ በቃ ትግል ምን እንደሆነ ለሌላው ምሳሌ የሆነ ሀገር ነው፡፡ ህዝቡ ጭቆናን በአፉ አይደለም በቃኝ ያለው፡፡ በተግባር ነው በቃኝ ያለው፡፡ ከጥቂት የጀልዱ ወረዳ ነዋሪዎች ነጋዴ በስተቀር ማንም ለመንግስት ግብር አልገበረም፡፡ ጀልዱ ዘንድሮ የልጆቿን ደም ነው የገበረችው፡፡ ልጆቿ ለሃገራቸው ብሎም ለኦሮምያ ነው መስዋዕት የሆኑት፡፡ ከ15 የሚበልጡ ልጆቿ ናቸው በአጋዚ ጥይት እንደ ፈሰሰ ቆሎ ሞት የለቀማቸው፡፡ ከ40 የሚበልጡት ለጆቿ ናቸው አካለ ስንኩል ሆነው የቀሩት፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው በእስር ቤት የማቀቁት፡፡ እስከአሁንም ዕየማቀቁ የሚገኙትም ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ እባብ ተቀጠቀጡ፡፡ እንስሳ እንኳን ክብር አለው፡፡ ለነገሩ ቀጥቃጮቹንም ገዳዮቹንም አልፈርድባቸውም፡፡ እንደ ፈረስ መብላት ለምደው እንደ ሰው ብሉ ሲባሉ ሆዳቸው ይርበዋል፡፡ መርሁ የሚለው “ግብር የሚከፈለው ለህዝቡ መሰረተ ልማት ሊሰራበት ነው“ ይላል፡፡ እነሱ ግን የሆዳቸውን መሰረተ ልማት ሞሉበት፡፡ ታድያ ለምንድነው ህዝቡ ለማይጠቅመው መንግስት ግብር የሚገብረው???? ህዝቡ በጣም ነው የተፀየፋቸው፡፡ የጀልዱን ካቢኔ አባላት ባየ ቁጥር ደሙ ነው የሚፈላው፡፡ ዲሮ ደሜ የሚባል አንድ ካቢኔ ነበረ፡፡ የዛሬ ወር አከባቢ ሱሉልታ ላይ ከዘላለም ጀማነህ ጋር በሙስና ተጠርጥሮ ቃሊቲ ይሁን ቂሊንጦ የተወረወረ፡፡ እሱ ነው የሙስና አባት የነበረው፡፡ የጀልዱን ወረዳ ህዝብና መሬት ጢባጢቤ ሲጫወትበት ከርሞ ለቺሳ ለሚባል ሰውዬ አስተላለፈ፡፡ ለቺሳ ሃዩ ወደ ምእራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር ሲገባ አጀማ ቶለሳ የመሬት ችርቻሮ ችቦውን ተቀበለው ፡፡ አጀማም የበኩሉን ድረሻ በደንብ ከወሰደ በኋል ፓርላማ ገባ፡፡ በፓርላማ ዘመኑ 1 ጥያቄ ብቻ ጠይቆ ወጣ፡፡ እሷንም የጠየቀው በቲቪ ለመታየት ፈልጎ ይመስለኛል፡፡ አጀማ በጣም ደፋር ነው፡፡ የሌባ ደፋር እሱን ነው ያየሁት፡፡ የጀልዱ ወረዳ አስተዳደር አስተዳዳሪ እያለ የመንግስት መኪና ወደ ስሙ ሊያዘዋውር ሞክሮ “የመንግስት መኪና ወደ ግል ማዞር አይቻልም” ብለውት መንገድ ትራንስፖርቶች ከለከሉት፡፡ እራሱን እንደ ፈጣሪ ይቆጥራል፡፡ ግን ምን ያደርጋል በወርሃ ህዳር 2008 መጨረሻ የጀልዱ ቄሮና ህዝብ ጀልዱን ሲያናውጧት ሱሪው ላይ ቅዘን ቀዘነ ተብሎ ይወራል፡፡ ይህቺን ወሬ እንኳን ያገኘነው ከሚቀርቡት ካቢኔዎች ነው፡፡ ይህ ሰውዬ ጀልዱ ከተማ ‘ካቢኔ ሰፈር’ የሚባለው ቦታ ወደ 1000 ካሬ የሚጠጋ መሬት አለው፡፡ መሬቱ ላይ ቤት ቢኖርበትም 700,000 ብር ሊሸጥ አስቦ ገዢ ስላጣ እሰካሁን ተቀምጧል፡፡ ለነገሩ ማን ከህዝብ ሌባ ይገዛል ብላችሁ ነው፡፡ አሁን አሁን የጀልዱ ካቢኔዎች አዲስ ፋሽን አምጥተዋል፡፡ ጀልዱ ያላቸውን ንብረት ሽጠው ወደ ሸገር አካባቢ ሌላ መሬት በመያዝ ወይንም በመግዛት ቤት ሰርቶ ወይንም ገዝቶ መኮብለል ጀምረዋል፡፡ በ2007ቱ የብላኔ ምርጫ የአጀማን የፓርላማ ወንበር ቆንጂት በቀለ ተረከበችው፡፡ በቲቪ መስኮት ለመታየት እንኳን እሷ አጀማን በለጠችው፡፡ አልፎ አልፎ በቲቪ ያው የለመድነውን ኢሃዲጋዊ ዲስኩር ስትደሰኩር እንሰማታለን፡፡ ማን ያውቃል Expired date የደረሰባቸውን ካቢኔዎች ዲሮ ደሜ ከእስርቤት ሆኖ ‘ኮልሚ ባክ’ ይልክላቸው ይሆናል:: ዘንድሮ በወርሃ መጋቢት ላይ ወደ 9የሚጠጉ ሰዎች የጀልዱ ወረዳ ካቢኔዎች ያደረጉትን ህገወጥ ድርጊት በማስረጃ አሰባስበው ወደ ኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንት ቢሮ ሄደው ሙክታር ከድርን አናግረውት ነበር፡፡ ሙክታርም መፍትሄ አለኝ ብሎ 3ሰዎች ወክሎ ወደ ጀልዱ ላከ፡፡ የተወከሉት ሰዎች በጎጆ ሽኩቴ እና ጮቢ ከተማ ህዝቡን ስብሰባ ጠርተው ሲያናግሩ ቆንጂት በቀለ ከሰብሳቢዎቹ ጋር መድረክ ላይ ነበረች፡፡ ይሁንና የተሰበሰበው ሰው ሁሉ ብሶቱን ሁሉም ካቢኔ ላይ ሲያወርድ ውሎ ሲበተን ሰብሳቢዎች መፍትሄ እንሰጣለን ብለው ወደ መጡበት ተመልሰው ቢሄዱም እስከ ዛሬ ድረስ አንድ ሁለት ሰው ከስልጣናቸው ላይ አስነስተው ወደ ዞን ሲልኳቸው የቀሩትን ግን እዛው በዛ አሸጓሸጓቸው፡፡ ያው ጉልቻ ቀያየሩ እንጂ ምንም አልለወጡም፡፡ የቀያየሩትንም የብላኔ ነበረ፡፡ ያን ሰሞን የተወሰኑት ካቢኔዎች ከቆንጂት በቀለ ጋር ሆድና ጀርባ ሆነው ነበረ፡፡ አኔ ግን ይቺ ነገር የፉገራ ይመስለኛል፡፡ ቆንጂት ለህዝቡ ወገነች ተብሎ ወሬ እንዲናፈስ የተፈለገ ይመስለኛል፡፡ እንደዛማ ባይሆን ኖሮ እነዛን ሁሉ ማስረጃዎች ይዘው ያንን ሁሉ የጀልዱ ወረዳ ካቢኔ ሌባ እስር ቤት መክተት ሲገባቸው ጉልቻ ብቻ ቀያይረው ሄዱ፡፡ ለነገሩ እነሱም ያው አይደሉ፡፡ ጉልቻዎች፡፡ ለነገሩ የህዝቡ ችግር ሌባ ካቢኔ እስረ ቤት ወርውሮ ሌላ ሌባ ካቢኔ እንዲፈጠር አይደለም፡፡ ጠቅላላ ስርአቱ ህዝቡን ዘላለማዊ ባርያ ስላደረገው ከነስሩ ነቅሎ መጣል ነው፡፡ ህዝብ አዋቂ ነው፡፡ ብዙ ደደብ ካቢኔ አይቻለሁ፡፡ እንደ ጀልዱ ወረዳ ካቢኔ ደደብ ግን አላየሁም፡፡ ለዛ ነው የጮቢ ሰዎች አይናችሁን ማየት አንፈልግም ብሎ ያባረራቸው፡፡ ይኸው ሽኩቴም በቀደም ዕለት አባረራቸው፡፡ የቦኒ ህዝብም እንደዛው፡፡
ከወርሃ መጋቢት በፊት ህዝቡ ፈንግሎ ሲጥላቸው ካቢኔዎቹ ይሰባሰቡና የኤክሰፓየር ዴታቸውን ሊያራዝሙ ፖሊስ ጣብያ ውስጥ እየተገነባ ካለው ህንፃ በጀት ላይ 700,000 ብር ቆንጥረው ለለቸሂሳ ሃዩ (የኣባቱን ስም እርግጠኛ አይደለሁም) ይሰጡታል፡፡ ከብሩ ውስጥ 200,000.00 ለራሱ እንዲወስድና የቀረውን 500,000.00 ግን ለዳባ ደበሌ እንዲሰጥና ዳባ ደበሌ ደግሞ የኦሮምያ ባለስልጣናትን እንዲጀነጅንላቸው ይነግሩታል፡፡ ነገሩ በሂደት ላይ እያለ ዳባ ደበሌን ቂሊንጦ ና ብላ ጠራችው፡፡ ጉዞ ወደ ቢሾሆፍቱ መስመር ሆነ፡፡ ከዛ ልክ ቃሊቲ ላይ ሲደርስ ቂሊንጦ ያሉት ሙሰኞች አጨብጭበው ተቀበሉት፡፡ ይህንን የ700,000 ብር ጉዳይ ቆንጂት በቀለ በደንብ ታቀዋለች፡፡ ከባንክ የወጣበትን ማስረጃ ሁላ አግኝታለች፡፡ ታድያ “የኛ ሀቀኛ” ከሆነች ለምን እነሱንም “ጉዞ ወደ ከቸሌ” አላስባለቻቸውም??? ለነገሩ ስለዚህ ብር ጉዳይ ሲጠየቁ “ለህንፃው ተቋራጭ የከፈልነው ገንዘብ ነው” ብለው መልስ ሰጥተው ነበር፡፡ እሺ እሱ ገንዘብ ለህንፃው ተቋራጭ ተከፈለ እንበል፡፡ ታድያ ቆንጂት በቀለ የህዝብ ተቆርቋሪ ከሆነች ለምንድነው እነ መገርሳ ፋና ያሁሉ የመሬት ዘረፋ ማስረጃ ተገኝቶባቸው በአቃቢ ህግ በኩል ክስ ያልተመሰረተባቸው????? ባጫ ደበሌ እስር ቤት ከገባ በኋለ እነዛ ከላይ የጠቀስኳቸው 9ሰዎች ሙክታር ከድርን አናግረው ከተመለሱ ከመጋቢት 23,2008 የሙክታር ወኪሎች የጎጆ ስብሰባ በኋላ ካቢኔዎች እርስ በርስ ይሰባሰቡና ሙክታር ከድር ጋር እራሳቸውን ሽማግሌ አድርገው ይሄዳሉ፡፡ ከዛ ሙክታርን “ህዝቡ ስልጣን ላይ የነበሩት ካቢኔዎች ያስተዳድረን ብሏል “ ብለው ይነግሩታል፡፡ እዚህ ላይ ነው በጣም ደደብ መሆነቸውን የሚያስመሰክሩት፡፡ እራሳቸው ካቢኔ ሆነው እራሳቸው ለራሳቸው ሽማግሌ ሲሆኑ፡፡ የድድብና ዲግሪ የሚሰጥ ቢሆን የጀልዱ ወረዳ ካቢኔዎች የድድብና ዲግሪ በማግኘት የሚወዳደራቸው አይኖርም፡፡ እኔ የምለው ለምን እነዚህ የዚች ሀገር ዩኒቨርሲቲዎች ለነዚህ ሰዎች የድድብና ዶክትሬት አይሰጣቸውም??? እንግዲህ የሙክታር መልስ ምንም ይሁን ምን እስከዛሬ ግማሹ ወደ ዞን አስተዳደር ሲሄድ የቀሩት ደግሞ እዛው ተሸጋሽገው የዝርፊያ ፕላናቸውን ቀጥለዋል፡፡ ለነገሩ የሙክታር መልስ ስልጣን ላይ ይቆዩ የሚል ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ያው ትንሹ ሌባ ከሌለ ትልቁ ሌባ መኖር አይችልም፡፡ የዛሬ ሳምንት የጎጆ ህዝብና የሽኩቴ ሕዝብ መንግስትን ተቃውሞ መንገድ ሲዘጋ ካቢኔዎቹ ሽኩቴ ሄደው ነበር፡፡ የሽኩቴ ህዝብ አዋርዶ ቢመልሳቸውም ተመልሰው ሽኩቴን ሊያስተዳድሯት ይፈልጋሉ፡፡ ህዝቡ ግን የሃጫሉ ሁንዴሳ ‘ሲንበርባዱ’ የሚለውን ዘፈን ጋብዞ ነው እንቁልልጬ ብሎ ያባረራቸው፡፡ ወንዳታ ሽኩቴ ብለናል፡፡ በቀደም ቅዳሜ ለታ ዳግም የሽኩቴ ህዝብ ጀግንነቱን አሳይቶአቸው አባረራቸው፡፡ አሁን ይህቺን ፅሁፍ እየፃፍኩኝ የዶዶላ ህዝብ ተቃውሞዉን እያሳየ ነው፡፡

ቸር እንሁን፡፡ ስለመብታችን ለመታገል ፖለቲከኛ መሆን አይጠበቅብንም!!!! አጆሌ ጀልዱ፡፡

::::::::
Caaluumaa Mangistuu – Duuti Hin Haftuu

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s