በኦህዴድ ውስጥ ፕወዛው ተጀመረ (Zehabesha)

በኦህዴድ ውስጥ ፕወዛው ተጀመረ | በከር ሻሌ (ኦቦ ገብረመድህን) የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ ተሾመ | ዳባ ደበሌ ትልቁን ስልጣን አጡ

በከር ሻሌ (ኦቦ ገብረመድህን)

https://i2.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/03/Beker-Shale.jpg(ዘ-ሐበሻ) ለሕወሃት አስተዳደር ራስ ምታት የሆነበትን የኦህዴድ አመራሮችን የመበወዙ ሥራ በይፋ ተጀመረ:: ከሳምንታት በፊት በዘ-ሐበሻ ድረገጽ የኦሮሞ ህዝብ በተለያዩ ከተሞች ያነሳውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ የኦህዴድ አመራሮች ጥርስ እንደተነከሰባቸውና በ ህወሓቶች እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ምንጮቿን ጠቅሳ መዘገቧ ይታወሳል::

የኦሮሞ ሕዝብ ያነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በሕወሓት መንግስት የኦሮሞን ህዝብ እንዲያረጋጉ ተልከው በየሚዲያው እየወጡ ሲያስተባብሉ የከረሙት የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኦቦ ዳባ ደበሌ ከስልጣናቸው ተነስተው ተዘዋውረዋል:: በርሳቸው ቦታ ላይም በሕወሓት መንግስት ተላላኪነታቸው “ኦቦ ገብረመድህን” የሚል ስም የተሰጠው አቶ በከር ሻሌ ይህን ቁልፍ ስልጣን መረከቡን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

አቶ በከር ሻሌ ከዚህ ቀደም የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ከመሆኑ በፊት በሚኒስትር ዴኤታነት የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆኖ ለወራት የሰራ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ተነስቶ ወደ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ተዛውሮ እንዲሰራ ተደርጎ የነበረው አቶ በከር፣ በጽሕፈት ቤቱ ለተወሰኑ ወራት በሚኒስትር ዴኤታነት ካገለገለ በኋላ የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሆኖ መሾሙ ይታወሳል::

ዳባ ደበሌ

https://i0.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/03/Daba-debele.jpgከግንቦት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ በሙስና ወንጀል በሕወሐት ተከሰው የታሰሩትን አቶ መላኩ ፈንታን ተክቶ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዳይሬክተር የተደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተመሣሣይ ሁኔታ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ባላወቀበት ሁኔታ የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆኖ በቀጭን ደብዳቤ ተሹሟል::

በቀጣይም ልክ እንደ ዳባ ደበሌ ሁሉ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ከየስልጣናቸው እየተነሱ ወደ ሌላ ቦታ እንደሚዘዋወሩ ምንጮቻችን ገልጸው ተረኞች ተራቸውን እየጠበቁ ሕወሓት ማድባቱን ተያይዞታል ብለውናል::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s