‹‹እንዴት አደርሽ ዉድ ሀገሬ?››

By Befekadu Moroda

Sofian Hussien's photo.

እንደለመደብኝ ዛሬ ማለዳ ከእንቅልፌ ተነሳሁና ኢተርኔት ዉስጥ ገባሁ፡፡ሁሌም እንደማደርገዉ ‹‹እንዴት አደርሽ ዉድ ሀገሬ?›› ለማለት፡፡
የዚያን ጀግና የበቀለ ገርባንና የወዳጄን የደጀኔ ጣፋን በወንበዴዎች እጅ መግባት ዜና አነበብኩና አሁንም እንደልማዴ ወደዉስጤ ማንባት ያዝኩ፡፡
በመሃል የአሥራ አንድ ዓመቷ ልጅ መጥታ አጠገቤ ቆማ ምን እንደሆንኩ ትጠይቀኛለች፡፡ የዶክተር መረራ ጉዲናንም ፎቶ አይታ ‹‹ምን ሁኖ ነዉ?›› አለችኝ፡፡
መረራ አሜሪካ መጥቶ ወደእኛ ግዛት ሲዘልቅ እኛ ቤት ስለሚያርፍ በደንብ ታዉቀዋለች፡፡ የእነበቀለን ታሪክና እንደገና መታሰር፣የዶክተር መረራንና የበቀለ ናጋን ተረኛ ታሳሪ መሆን ነገርኳት፡፡
‹‹ለምን ያንን ሀገር ትተዉ አሜሪካ አይመጡም? እዚህ ማንም አይካቸዉም?›› አለች፡፡
እንዲሁ አፌ ላይ መጣና‹‹ሕዝቡስ?›› አልኳት

‹‹ሕዝቡስ ለምን ሀገሩን ጥሎላቸዉ አይወጣም፡፡ ያኔ ማንን ይገድላሉ? ማንን ያስራሉ?›› አለችኝ፡፡
ቀላል ጥያቄ አይደለም፡፡ምናልባትም ዛሬ ወገኞቼ ያላቸዉ ሦስተኛ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል አሰብኩ፡፡ሀገሩን ጥሎላቸዉ ነቅሎ መዉጣት፡፡ ያኔ ማንን ይገድላሉ? ማንን ይገርፋሉ? ማንን ያስራሉ?
ይኼ ምርጫ እንዲህ እንደእኔ ወሬና እንደልጄ ሐሳብ ቀላል ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር?
ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ ሕፃናት ልጆቹን እንደበግ ግልገል እየነጠቀዉ የሚገድል፣ነፍሰጡሮችን የሚረሽን ፣አዋቂዎቹን እየለቀመ የሚገርፍና የሚያስር ሀገር በቀል ጨካኝ ቅኝ ገዢ ይዘባበትበታል፡፡ ዛሬ ኦሮሞ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ በባሰ ሁኔታ የባርነትና የዉርደት ቀንበር ተሸካሚ ሆኗል፡፡የዉርደቱን ደረጃ የላቀ የሚያደርገዉ ደግሞ ይህ ሕዝብ እየተገዛ ያለዉ በጥቂት ወሮበላ የአንድ መንደር ወንበዴዎች መሆኑ ነዉ፡፡

ዛሬ ኢትዮጵያ ፣ሕዝብ ያለመንግሥት የሚኖርባት ሀገር ናት፡፡ጥቂት ጠመንጃ የታጠቁ ፣እርስ በእርሳቸዉ እንኳን የማይግባቡ፣ በቡድን በቡድን ተከፋፍለዉ እንደጅብ የሚጠባበቁ ዱሪዬዎች በሕዝብ ላይ የሚኮሱባት ሀገር ናት የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ፡፡
እነርሱ ይህን ያህል ሥርዓተ አልበኛ ሆነዉ ሲቀብጡ፣ተመሳሳይ የጭቆና ቀንበር የተሸከሙ፣ አሳርና ፍዳ የሚቁሙ የሀገሪቱ ዜጎች ግን ዛሬም የታሪክ ድሪቶ እየዘመዘሙ እርስ በእርስ ይሻኮታሉ፡፡ ይህ ወሳኝ ጊዜ ነዉ፤በግፍ አገዛዝ ሥር ያለን ዜጎች፣ነባር ቅራኔዎቻችንን ትተን ወቅቱ ታሪክ በጫነብን የጋራ ጠላት ላይ በአንድነት መነሳት እስከአልቻልን ድረስ ከጩኸትና ከባዶ ፉከራ ያለፈ ፋይዳ አይኖረንም፡፡

ዛሬ ተራዉ የኦሮሞ ነዉ፡፡ እንደሐሳባቸዉ ከተሳካላቸዉ ኦሮሞን አንበርክከዉ ወደአማራ ያልፋሉ፡፡አማራ ላይ አይቆሙም፡፡ ሲዳማን ፣ሀዲያን፣ጋሞን፣ጉራጌን፣አኙዋን…በየተራ ያንበረክኩና አገዛዙን ለልጅ ልጆቻቸዉ ያስተላልፋሉ፡፡
በተለይም፣ ትናንት እሩቅ ለሩቅ ሆነህ ድንጋይ ስትወራወር፣ሸር ስትደዋወር የነበርከዉ የኦሮሞና የአማራ ‹‹ኤሊት›› ተብዬ ፅንፈኛ ሁሉ፣ ወደሕሊናህ ትመለስ ዘንድ፣የጋራ መድረክ ፈጥረህ ትነጋገር ዘንድ ጊዜና ታሪክ እያቀረበ ያለዉን ጥሪ ስማ፡፡
ይህን ማድረግ ካልቻልክ ደግሞ ድንፋታህ አቁመህ፣ባዶ ኩራትህን በልክ ከርክመህ፣ ሰጥ ለጥ ብለህ ለወያኔ ተገዛ፡፡ ሕዝቡንም አስገዛ፡፡ ወሬ…ጉራ…

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s